የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የሕክምና ላቦራቶሪ አሰሰሮች ዓመታዊ ካሊብሬሽን እየተካሔደ ነው
ዓመታዊ የአሰሰሮች ካሊብሬሸን ዛሬ በአዳማ ሲጀመር የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ እንደተናገሩት የአክሪዲቴሽን ሥራ ለአጭር ጊዜ ከተውት በርካታ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ሊያመልጡ ይችላሉ
በመሆኑም አክሪዲቴሸን ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ሁል ጊዜ ራሱን ማብቃትና በስራ ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባው ጠቁመው ዓመታዊ የአሰሰሮች ካሊብሬሽንም የሚዘጋጀው በስራ ሂደት የገጠሙ ችግሮችን በጋራ መድረክ ለመፍታት እንደሆነ አመልክተዋል
የአገልግሎቱ የጥራት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ መሰረት ተሰማ በበኩላቸው እንደተናገሩት ዓመታዊ ካሊብሬሽን ዋና ዓላማ የአገልግሎቱ የትርፍ ሰዓት አሰሰሮች በዓመቱ ውስጥ ስራቸውን ሲሰሩ ያጋጠሙዋቸውን ተጨባጭ ችግሮች በመለየት ለችግሮቹ የጋራ መፍትሔ መስጠት ነው
ዓመታዊ የአሰሰሮቹ ኮንፍረንስ በተጨማች ክፍተቶች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የተናገሩት የጥራት ሥራ አስኪያጅዋ አሰሰሮቹ ከተጨባጭ ችግሮቹን በመነሳት ለተመሳሳይ ችግሮች ተመሳሳይ መፍትሔ መስጠት ይገባቸዋል
የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ሲሰጥ አሰስመነት በሚሰራበት ወቅት ለሚገጥሙ ችግሮች አሰሰሮች ምን አይነት መፍትሔ እንደሚሰጡ፣ አሰስመንት ከመጀመሩ አስቀድሞ በመክፈቻ ስብሰባዎች/ Opening Meeting/ ፣በመዝጊያ ስብሰባዎች/ Closing Meeting/ ከቡድን መሪው ምን አይነት ብቃትና ሊከተላቸው የሚገቡ ጉዳዮችንም በጋራ ውይይት ሊደረግባቸው እንደሚገባው አመልክተዋል
ባለሙያዎቹ በስራ ሂደት ባጋጠሙዋቸው ተጨባጭ ችግሮች ላይ የቡድን ውይይት ያደረጉ ሲሆን የቡድን ውይይቱ ለተመሳሳይ ችግሮች ወይንም በስራ ላይ ለሚገጥሙ አንድ አይነት ችግሮች ተመሳሳይ መፍትሔ ለመስጠት በሚችሉበት ሁኔታ ላይም መክረዋል