News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የሕክምና ላቦራቶሪ አሰሰሮች ዓመታዊ ካሊብሬሽን እየተካሔደ ነው

ዓመታዊ የአሰሰሮች ካሊብሬሸን ዛሬ በአዳማ ሲጀመር የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ እንደተናገሩት የአክሪዲቴሽን ሥራ ለአጭር ጊዜ ከተውት በርካታ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ሊያመልጡ ይችላሉ

በመሆኑም አክሪዲቴሸን ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ሁል ጊዜ ራሱን ማብቃትና በስራ ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባው ጠቁመው ዓመታዊ የአሰሰሮች ካሊብሬሽንም የሚዘጋጀው በስራ ሂደት የገጠሙ ችግሮችን በጋራ መድረክ ለመፍታት እንደሆነ አመልክተዋል

የአገልግሎቱ የጥራት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ መሰረት ተሰማ በበኩላቸው እንደተናገሩት ዓመታዊ ካሊብሬሽን ዋና ዓላማ የአገልግሎቱ የትርፍ ሰዓት አሰሰሮች በዓመቱ ውስጥ ስራቸውን ሲሰሩ ያጋጠሙዋቸውን ተጨባጭ ችግሮች በመለየት ለችግሮቹ የጋራ መፍትሔ መስጠት ነው

ዓመታዊ የአሰሰሮቹ ኮንፍረንስ በተጨማች ክፍተቶች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የተናገሩት የጥራት ሥራ አስኪያጅዋ አሰሰሮቹ ከተጨባጭ ችግሮቹን በመነሳት ለተመሳሳይ ችግሮች ተመሳሳይ መፍትሔ መስጠት ይገባቸዋል

የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ሲሰጥ አሰስመነት በሚሰራበት ወቅት ለሚገጥሙ ችግሮች አሰሰሮች ምን አይነት መፍትሔ እንደሚሰጡ፣ አሰስመንት ከመጀመሩ አስቀድሞ በመክፈቻ ስብሰባዎች/ Opening Meeting/ ፣በመዝጊያ ስብሰባዎች/ Closing Meeting/  ከቡድን መሪው ምን አይነት ብቃትና ሊከተላቸው የሚገቡ ጉዳዮችንም በጋራ ውይይት ሊደረግባቸው እንደሚገባው አመልክተዋል

ባለሙያዎቹ በስራ ሂደት ባጋጠሙዋቸው ተጨባጭ ችግሮች ላይ የቡድን ውይይት ያደረጉ ሲሆን የቡድን ውይይቱ ለተመሳሳይ ችግሮች ወይንም በስራ ላይ ለሚገጥሙ አንድ አይነት ችግሮች ተመሳሳይ መፍትሔ ለመስጠት በሚችሉበት ሁኔታ ላይም መክረዋል 

የሕክምና ላቦራቶሪ አሰሰሮች አመታዊ ካሊብሬሸን እየተካሔደ ነው