News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ተደራሽነቱ በማስፋት አገልግሎት አሰጣጡን በማሳደግ ላይ ይገኛል፡፡

ጥቅምት 27 ቀን 2016ዓ.ም

የአፍሪካ አክሬዲቴሽን ትብብር በኦክቶበር 2023 በኬንያ ናይሮቢ ከተማ ባደረገው 14ኛው ጠቅላላ ጉባኤ፤ ቀደም ሲል በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ስምንት አባላትን የያዘ የራሱን የግምገማ ቡድን በመላክ አገልግሎቱ የሚከተለው የአለም አቀፍ የአሰራር ስርዓት፣ የአመራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ብቃት፣ እንዲሁም ተቋሙ አክሬዲት ካደረጋቸው ተቋማት ወካይ ናሙና በመውስድ ለ5 ቀናት ካደረገው ግምገማ ውጤት በመነሳት ተቋማችን በሕክምና ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን፣ በፍተሻ ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን፣ በኢንስፔክሽን እና በጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ቀደም ሲል የነበረውን ዓለም አቀፍ ዕውቅና እንዲቀጥል እና በተጨማሪም በሁለት ወሰን ማለትም፤ በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ እና በምርት ሰርቲፊኬሽን አለም አቀፍ እውቅና ሰጥቷል፡፡

ይህም አገልግሎቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘባቸውን ዘርፎች ወደ ስድስት አሳድጎታል፡፡

ይህ አለም አቀፍ ዕውቅና፤ የተስማሚነት ምዘና ተቋማት ብቃታቸውን በማረጋገጥ የአገራችንን ገቢና ወጭ የንግድ ስርዓት ለማሳለጥና የምርትና የአገልግሎቶችን ጥራት ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም የዜጎችን ጤናና ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ ድርሻ ያለው  ነው፡፡

በመሆኑም ዕውቅናው እንደ ተቋም ብቻ ሳይሆን እንደ አገር ትልቅ ስኬት ነው፡፡

የተቋሙ አለም አቀፍ ዕውቅና እየጨመረ መምጣትና የሚሰጣቸው የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ወሰን መስፋት፤ የአገራችን የተስማሚነት ምዘና ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት እና ሌሎች በካሊብሬሽን አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ተቋማት፤ ቀደም ሲል የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ለማግኘት ለውጭ ድርጅቶች ያወጡ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛርን ከማዳኑም በላይ፣ መንግስት ለጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ተቋማቱን በመሳሪያና በሰው ሃይል ለመገንባት የሰራቸው ስራዎች ተቋማቱ ለሚሰጡት አገልግሎት አለም አቀፍ ተቀባይነታቸው እንዲጨምር ያደረገ መሆኑ፣ እንዲሁም እንደ አገር በአህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለሚኖረው የንግድ ውድድር ተደማሪ አቅም እየተፈጠረና ለተጀመረው የብልፅግና ጉዞ በመንግስትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ትልቅ መሰረት እየተጣለ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡  

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ተቋማችን ባደረገው የረጅም ጊዜ ግምገማ፣ በዛሬው ዕለት ሁላችንም የምንኮራበት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በማይክሮ ባዮሎጂ ላቦራቶሪ የአክሬዲቴሽን እውቅና የሰጠ ሲሆን፤ ይህም አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተጓዥ መንገደኞቹ የሚያቀርባቸው የምግብና የመጠጥ አገልግሎቶች ደህንነታቸው የተረጋገጠ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ፡፡

በተመሳሳይ የሕብረተሰባችንን ጤናና ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚሰሩ የጤና ተቋማት ውስጥ ለአንጋፋው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጅን ኤክስፐርት፣ በማይክሮ ባዮሎጂ እና በኤ ኤፍ ቢ ማይክሮ ስኮፕ ላቦራቶሪዎች፤ ለመቱ አጠቃላይ ካርል ሆስፒታል በቫይራል ሎድ፤ ለቅ/ገብርኤል አጠቃላይ ሆስፒታል በክሊኒካል ኬሚስትሪና ሄማቶሎጂ ላቦራቶሪዎች የሶስተኛ ወገን የብቃት ምስክርነት ወይም የአክሬዲቴሽን እውቀና የሰጠ ሲሆን፤ የሳቢያን አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የጨለንቆ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ገ/ጻዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል በጅን ኤክስፐርት ላቦራቶሪዎች ብቁ ሆነው በመገኘታቸው የአክሬዲቴሽን እውቅና ሰርቲፊኬት አግኝተዋል፡፡

በተያያዘም የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት በሥራ አመራር ሥርዓት ወሰን በማስፋት በአካባቢ ሥራ አመራር ሥርዓት፣ በምግብ ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት እና በሥራ ላይ ጤናና ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት እንዲሁም የብለስ የግብርና ምግቦች ላቦራቶሪ ኃ.የተ.የግል ድርጅት በምርት ሰርቲፊኬሽን አክሬዲቴሽን እውቅና አግኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለአገር ውስጥ ተቋማት ከሚሰጠው የአክሬዲቴሽን አገልገሎት በተጨማሪ በቅርቡ በህንድ አገር የሚገኝ የጥራት ቁጥጥር ሰርቲፊኬሽን ተቋም ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ባደረገው ግምገማ፤ ተቋሙ ባመለከተባቸው የአገልግሎት ወሰኖች  ማለትም በጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ በአካባቢ ሥራ አመራር ሥርዓት፣ በምግብ ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ በሥራ ላይ ጤናና ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት እና በኢንፎርሜሽን ሥራ አመራር ሥርዓት ብቁ ሆኖ በመገኘቱ የሰርቲፊኬሽን አክሬዲቴሽን እውቅና ተሰጥቶታል፡፡

ይህም አገልግሎቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ሰጪ ተቋም ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራና ራዕይ እውን እየሆነ መምጣቱን ያረጋግጣል፡፡

የዜና መግለጫ