News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለ11 ተቋማት የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ሰጠ ። አገልግሎቱ የተሰጠው በኢንስፔክሽን ፣ በሰርተፍኬሽን ፣በፍተሻ እና ካሊብሬሽን እንዲሁም በህክምና ላብራቶሪዎች ዘርፍ ሲሆን በISO/IEC 17065/IAF/EAS መስፈርቶች መሰረት በምርት ሰርተፍኬሽን ዘርፍ የኢተዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት እንደ ሀገር የመጀመሪዉን የአክሪድቴሽን አገልግሎቱን አግኝ~ል።

እንዲሁም በISO/IEC 17025/ILAC/EAS አስገዳጅ መስፈርቶች መሰረት የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክስዮን ማህበር ፣ የኤ. ስ .ጅ .ኤስ እና አይሲቲ ሰርቢስ ፒኤልሲ ሲ. አር . ሲ ሶፍት ላይን ላብራቶሪ ፣ በግሉ ዘርፍ የዊነር ኢንጅነሪንግ እና ካሊብሬሽን ላብራቶሪ እንደ ሀገር የመጀመሪዉን የአክሪድቴሽን አገልግሎቱን፣ የኢትዮጵያ ቴክስታይል ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት እና ብለስ አግሪ ፉድ ላብራቶሪ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት በፍተሻ ላብራቶሪ አገልግሎቱን አግኝተዋል

እንዲሁም በISO/IEC 17020/ILAC/EAS አስገዳጅ መስፈርቶች መሰረት የኢተዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት እና ብለስ አግሪ ፉድ ላብራቶሪ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት በኢንሰፔክሽን ዘርፍ ቀድመው ካገኑት በተጨማሪ ወሰን በማስፋት አገልግሎቱን አግኝተዋል ።

በተጨማሪም በISO 15189/ILAC/EAS አስገዳጅ መስፈርቶች መሰረት የሸጋዉ ሞጣ ጀነራል ሆስፒታል ፣ የአማራ ፐብሊክ ሐልዝ ኢንሰቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ ፣የዲላ ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የብሔራዊ የሳንባ ነቀርሳ እና የአለም ከተማ እናት ሆስፒታል በህክምን ላብራቶሪ ዘርፍ የአክሪድቴሽነ ሰርተፍኬት የወሰዱ ተቋማት ናቸዉ ።

ሰርቲፊኬቱን የሰጡት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ እንዳሉት የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ንግድ እንዲስፋፋ ፣ እንዲዘምን እንዲሁም ህጋዊ አሰራር እንዲሰፍን የሕብረተሰቡ ጤና፣ደህንነት፣አካባቢ እንዲጠበቅ ማድርግ እና ፍትሃዊ የግብይት ስርአት እንዲሰፍን የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድርግ እና በአገር ውስጥ የሚደረግ የግብይት ቁጥጥርና መንግስታዊ ውሳኔዎች ውጤታማ፣ተቀባይነት እና ተአማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ አገልግሎቱ በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል ።

በተለይም ምርት እና ምርታማነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን ከጥራት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በመፈታት ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶች እና አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ለማድረግ የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት ሚና እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለዉ በመረዳት ለዘረፉ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰራ መሆኑን አክለዋል።

በመሆኑም ከጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በሚንስተሮች ምክር ቤት በተሻሻለዉ ደንብ ቁጥር 421 /2010 መሰረት ለተስማሚነት ምዘና ተቋማት በህክምና ላበራቶሪዎች ፣ በፍተሻ ላቦራቶሪዎች እና ካሊብሬሽን ላብራቶሪዎች ፣ በኢንስፔክሽን እና ሰርትፍኬሽን ገለልተኛ በመሆን የ3ኛ ወገን የቴክኒካል ብቃት ምስክርነት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

ተቋሙ የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ እና በብቃት ለመወጣት በዓለም አቀፍ እውቅና ባገኘባቸው በሁሉም ወሰኖች ተቀባይነት ያለው የአክሬዲቴሽን አገልግሎት መስጠት ችሏል ሲሉ ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡