News

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለሁለት ወላጅ አልባ ሕጻናት የትምህርት መገልገያ ደብተር እና ቦርሳ እንዲሁም ጫማና ልብስ ድጋፍ አደረገ፡፡

በየአመቱ እንደሚደረገው የዘንድሮም የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ሊገለገሉበት የሚያስችላቸውን ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

አገልግሎት መ/ቤቱ በተጨማሪም ለእያንዳንዳቸው 1,500.00 /አንድ ሺ አምስት መቶ  ብር  የገንዘብ ድጋፍ ሰጥቷል፡፡

 ሕፃናቱ የ2ኛ ክፍል ተማሪ እያሉ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፍ እያደረገላቸው ያሉት ተማሪዎች ሲሆኑ በዓመቱመጀመሪያና በዓመቱ አጋማሽ ላይ እገዛዎችን ሲያደርግላቸው ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ሁለቱም ሴት ተማሪዎች ወደ 10ኛ ክፍል ተዛውረዋል፡፡

ተማሪዎቹ በትምህርታቸው እንዲ ጠነክሩ እና እንዲበረታቱ በቀጣይም አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፉን እንደሚቀጥል ጠቅሰው የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር /ተወካይ/ ወ/ሮ መሠረት ተሰማ ተናገሩ፡፡

አገልገሎት መ/ቤቱም  ተማሪዎቹ በርትተው ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ ድጋፍ እንዳማያቋርጥም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለሚያሳድጋቸው ሁለት ወላጀ አልባ ህፃናት ድጋፍ አደረገ