News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ከግሎባል ኤሲአይ (Global ACI) ጋር ያለውን የባለብዙ ወገን የጋራ እውቅና ስምምነት በፊርማ አደሰየኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የአለምአቀፍ ዕውቅና ትብብር (GLOBAL ACCREDITATION COOPERATION INCORPORATED) ሙሉ አባል ሆነ::በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ግዜ ከነሐሴ 24-29/2017 ዓ.ም እየተካሄደ የሚገኘው ‘የኢትዮጵያ ይግዙ ‘ የንግድ ሳምንት ላይ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ለጎብኝዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡Call for Healthcare Accreditation Surveyorየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የኢስኳ ISQua ይፋዊ ሙሉ አባል በመሆን አለም አቀፍ የጤና ዘርፍ አክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት መስጠት የሚያስችለውን እውቅና አጊንቷል።የኢትዮጵያ አክሬድቴሽን አገልግሎት 17ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን አከበረ።የመ/ቤቱ ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱጥራትን ማስጠበቅ የሁሉም አካላት አንገብጋቢ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት በአለም አቀፍ አክሬዲቴሽን እና በአፍሪካ አክሪዲቴሽን ኮኦፐሬሽን ግምገማ ከጥቅምት 15-17 ቀን 2014ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን የተገኙት 02 ክፍተቶች እና 09 አስተያየቶች የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ በአፍሪካ አክሪዲቴሽን ኮኦፐሬሽን ካውንስል ከግንቦት 24-25 2014ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በAFRAC እና ሐምሌ 1 ቀን 2014 በIAF MLA signatory ተቀባይነት አግኝተናል፡፡

ይህ ስኬት ለመስሪያቤቱም ለሀገርም የሚያስገኘው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ስለሆነ የተገኘውን እውቅና ምክንያት በማድረግ ሀምሌ 15 ቀን 2014ዓ.ም የባለሙያ ስነምግባር ላይ አቶ አዱኛ አብዲሳ እና በስራ አካባቢ ደህንነትና ላይ በአቶ ዘውዱ ገ/ሚካኤል ስልጠና የተሰጠ ሲሆን እንዲሁም የምስጋና ፕሮግራም ተጋባዥ እንግዶች አጠቃላይ የአገልግሎቱ ሰራተኞች በተገኙበት በኣዳማ ሂልሳይድ ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በመክፈቻ ንግግር ላይ የአገልግሎቱ የጥራት ስራ አስኪያጅ እና በጊዜያዊነት መስሪያቤቱን እየመሩ ያሉት ወ/ሮ መሰረት ተሰማ እንደገለጹት ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በሚሰጣቸው የአክሬዲቴሽን ወሰኖች በፍተሻ ላብራቶሪ ISO/IEC 17025፤በህክምና ላበራቶሪ ISO 15189 ፤በኢንስፔክሽን ISO/IEC 17020 በአለም አቀፍ ማለትም ILAC/AFRAC MRA እውቅና ያገኘ ሲሆን መስሪያቤቱ በ2014 በሲስተም ሰርተፊኬሽን ISO/IEC 17021-1 and ISO/IEC 17021-3 quality management system(QMS) to ISO 9001 በአለም አቀፍ አክሬዲቴሽን እና በአፍሪካ አክሪዲቴሽን ኮኦፐሬሽን ግምገማ ከጥቅምት 15-17 ቀን 2014ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ላለፉት ወራቶች የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ በአፍሪካ አክሪዲቴሽን ኮኦፐሬሽን ካውንስል ከግንቦት 24-25 2014ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በAFRAC እና ሐምሌ 1 ቀን 2014 በIAF MLA signatory ተቀባይነት እውቅና ያገኘ መስሪያቤት ነው፡፡

በዚህም ስኬት ሊመሰገኑ የሚገባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፤ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለጥራት መሰረተ ልማት የአለም ባንክ ፕሮጀክት የምስጋና ሰርተፊኬት የተበረከተላቸው ሲሆን፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በተዋረድ ሁሉም የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ተመስጋኝ ናቸው ብለዋል፡፡በቀጣይም ግንቦት 2015 ዓ.ም በሚደረገው የአለም አቀፍ ግምገማ እውቅናውን ማስቀጠል እና አዲስ የምናሰፋቸው ወሰኖች መኖሩን ተገንዝበን የበለጠ መጠንከርና መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ተያይዞም የቀድሞው የመስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍሰሃ፤ የቀድሞው ምክትል ዋና ዳይሬክትር አቶ ጌትነት ጽጌ መላክ እና የቀድሞው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ ክብሩን የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት በሲስተም ሰርተፊኬሽን ISO/IEC 17021-1 and ISO/IEC 17021-3 quality management system (QMS) to level-5 ISO 9001 በአለም አቀፍ አክሬዲቴሽን ፎረም እና በአፍሪካ አክሪዲቴሽን ኮኦፐሬሽን እውቅና አገኘ፡፡