አገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ ወደ ጥራት ለማምጣት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ደፋ ቀና ማለት ከጀመረች ቆይታለች። ይህን ውጥን ለማሳካት እንዲረዳትም ገለልተኛ የሆነ የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የሚሰጥ ጥራት አረጋጋጭና እውቅና ሰጪ ተቋም የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎትን አደራጅታለች።
ተቋሙም በዓለም አቀፍ ደረጃ ISO/IEC 17011 እንዲሁም በዓለም አቀፍ የላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ትብብር /International Laboratory Accreditation Cooperation-ILAC/ እና በዓለም አቀፍ አክሬዲቴሽን ፎረም (International Accreditation Forum (IAF) ፖሊሲ መሰረት የተቋቋመ ነው።
በዚህም መሰረት ለተስማሚነት ምዘና ተቋማት ማለትም ለፍተሻና ካሊብሬሽ ላቦራቶሪ፣ ለህክምና ላቦራቶሪ፣ ለኢንስፔክሽን እና ለሰርተፊኬሽን ተቋማት የአክሬዲቴሽን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። የኢትዮጵያ አክሬዲቴሸን አገልግሎት የተቋቋመው በ2003 ዓ.ም ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ እምርታን ማስመዝገብ ችሏል። እንደ ተቋምም ስኬታማ ሆኗል። አገልግሎቱ ለሌሎች ተቋማት ዓለም አቀፍ ምስክርነት የሚሰጥ በመሆኑ ራሱ አስቀድሞ ዓለም አቀፉን ደረጃ ሊኖረው የግድ ይላል። በመሆኑም በፍጥነት ዓለም አቀፍ አሰራሮችን በመከተልና በመተግበር ዓለም አቀፍ ተቀባይነትም ያገኘ ተቋም ነው።
ባለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ውስጥ በሚሰጣቸው የአክሪዴቴሽን አገልግሎቶች በተለያዩ ወሰኖች የዓለም አቀፍ እውቅናን አግኝቷል። የኢትዮጵያ አክሬዲቴሸን አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን መሰረት ያደረገ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት አዲስ በተገነባው ውብ የጥራት መንደር ውስጥ በፍተሻ ላቦራቶሪ፣ በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ፣ በሕክምና ላቦራቶሪ፣ በኢንስፔክሽን፣ በምርት ሰርቲፊኬሽን እንዲሁም በአሰራር ሥርዓት ሰርተፍኬሸን ዓለም አቀፍ እውቅና በማግኘት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት
Once Accredited Accepted Everywhere !
+251-116671247/0116670995
Web: www.eas-eth.org
Facebook: https://web.facebook.com/ethioEAS/
Twitter : https://x.com/Eas_Ethio
Email: info@eas-eth.org
P.O.Box – 3898

