News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ከግሎባል ኤሲአይ (Global ACI) ጋር ያለውን የባለብዙ ወገን የጋራ እውቅና ስምምነት በፊርማ አደሰየኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የአለምአቀፍ ዕውቅና ትብብር (GLOBAL ACCREDITATION COOPERATION INCORPORATED) ሙሉ አባል ሆነ::በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ግዜ ከነሐሴ 24-29/2017 ዓ.ም እየተካሄደ የሚገኘው ‘የኢትዮጵያ ይግዙ ‘ የንግድ ሳምንት ላይ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ለጎብኝዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡Call for Healthcare Accreditation Surveyorየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የኢስኳ ISQua ይፋዊ ሙሉ አባል በመሆን አለም አቀፍ የጤና ዘርፍ አክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት መስጠት የሚያስችለውን እውቅና አጊንቷል።የኢትዮጵያ አክሬድቴሽን አገልግሎት 17ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን አከበረ።የመ/ቤቱ ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱጥራትን ማስጠበቅ የሁሉም አካላት አንገብጋቢ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ሠራተኞች በሃገር ውስጥ የያዛቸውን ዓላማዎች ለማሳካትና ዓላም አቀፍ ተቀባይነቱን አስጠብቆ ለመቀጠል የተቋሙ ባለሙያዎች ራሳቸውን ወቅቱ ከሚጠይቀው ሙያዊ ብቃት ሊኖራቸው እንደሚገባ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ተናገሩ

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አርአያ ፍስሃ ለተቋሙ ሰራተኞች በተለወጡ የተቋሙ ሰነዶችና መመሪያዎች ላይ በተዘጋጀው ስልጠና መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት አክሬዲቴሽን  አንድ ጊዜ አውቄአለሁ ተብሎ የሚተው ተግባር ሳይሆን ሠራተኛው በየጊዜው አቅሙን ሊገነባ ይገባል

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን  አገልግሎት ዓላማዎችን ለማሳካት ዋነኛ ቁልፍ ጉዳይ የተቋሙ ባለሙያዎች ብቃትና ለሥራ ያላቸው ዝግጁነት እንደሆነ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም ተቋሙ ባለፉት ዓምስት አመታት በርካታ ስልጠናዎች መስጠት መቻሉን ጠቁመዋል

ተቋሙ አሁን በ2014ዓ.ም የፌዴራል መንግስት አዲስ አደረጃጀት ተከትሎ የተቋሙ ስያሜ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን  አገልግሎት በሚል በመስተካከሉ ተቅሙ ሲሰራባቸው የነበሩ በርካታ ሰነዶችን የማስተካከል ሥራም እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል

 ሠራተኛው ለተገልጋዮቹ ብቃት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ ራሱ ብቃቱን በየጊዜው እያሳደገ ሊሄድ እንደሚገባ ተናገረዋል

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን  አገልግሎት በ2014ዓ.ም የያዛቸውን እቅዶች ለማሳካት የሰራተኛው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አቶ አርአያ ጠቁመው በስልጠናው የተቋሙን የዘጠኝ ወር የሥራ አፈጻጻም በመገምገም በቀሪዎቹ ሶስት ወራት ያልተፈጸሙ ተግባራት በፍጥነት በማከናወን የዓመቱን እቅድ ለማሳካት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል

ስልጠናው የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን  አገልግሎት የሚሰራበትን ፖሊሲ ማንዋል፣የሠራተኞች የተለያዩ ደንቦች፣እንዲሁም የሥራ ስነምግባርና የተቋሙ የዘጠኝ ወር አፈጻጻም ላይ በመወያየት በቀጣይ ሶስት ወር ቅድሚያ በሚሰጣቸው ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል

የተቋሙን ዓላማን ለማሳካት የተቋም ባለሙያዎች ራሳቸውን በሙያ ሊያሳድጉ ይገባል