News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሸን አገልግሎት የአክሬዲቴሽን ተጠቃሚ ለመሆን ለተቃሙ ማመልከቻ ላቀረቡና የተቀመጠውን ዓለም አቀፍና ብሔራዊ መስፈርቶች ላሟሉ ለስድስት የሕክምና፣ ለሶስት የፍተሻ ላቦራቶሪ፣ ለሶስት የኢንስፔክሽን እና ለአንድ የሰርቲፍኬሽን ተቋም የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ሰጠ፡፡

ተቋሙ ዛሬ ግንቦት 9ቀን 2014ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደው የሰርቲፍኬት አሰጣጥ ስነስርአት ላይ የአክሬዲቴሸን አገልግሎት የሰጣቸው ቀደም ሲል ለተቋማችን የአክሪዲቴሽን ማመልከቻ አስገብተው ሰነዳቸው የተገመገመ፣ የመስክ ግምገማው የተሰራላቸውና በአሰራሩ መሰረት የነበረባቸውን ክፍተቶች አስተካክለው ለተቋማችን ያቀረቡ ሲሆን በአክሪዲቴሽን አጽዳቂ ኮሚቴ አክሪዲትድ እንዲሆኑ የተወሰነላቸው ናቸው ፡፡

በሕክምና ላቦራቶሪ አክሪዲቴሽን ዘርፍ ISO 15189፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ላቦራቶሪ በሁለት የፍተሻ ወሰኖች ማለትም በሔማቶሎጂ እና ክኒሊካል ኬሚስትሪ የፍተሻ ወሰኖች፣የደብረማርቆስ አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ላቦራቶሪ፣ የቢሸፍቱ ሆስፒታል የሕክምና ላቦራቶሪ ፣የእንጅባራ አጠቃላይ ሆስፒታል የሕክምና ላቦራቶሪ፣የዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ላብራቶሪ  በአንድ የፍተሻ ወሰን በጅን ኤክስፐርት የአክሪዲቴሽን አገልገሎት ያገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሔማቶሎጂ የሕክምና ላቦራቶሪ በአንድ የፍተሻ ወሰን በሔማቶሎጂ  የፍትሻ ወሰን የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በፍተሻ ላቦራቶሪ የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ የሆኑት ISO/IEC 17025 የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ቀደም ሲል በሞሎኪዩላር፣ በሴሮሎጂ እና በባክቶሮሎጂ የአክሬዲቴሽን  የነበሩ ሲሆን አክሪዲቴሽን ተጠቃሚ የሆኑባቸውን  ወሰኖች አስፍተዋል፣ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ቀደም ሲል የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ ከነበረባቸው የኬሚካል በ83 ፓራሜትሮች፣፣ማይክሮ ባዮሎጂ በ11 ፓራሜትሮች፣ጨርቃጨርቅ በ5 ፓራሜትሮች፣ እንዲሁም ኤሌክትሪካል በ5 ፓራሜትሮች ላቦራቶሪዎችን የወሰን ማስፋት የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ የሆነ ሲሆን መካኒካል የፍተሻ ዘርፍ ደግሞ አዲስ የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኗል፣የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ የቴክስታይልና ፋሽን ኢንስቲትዩት በጨርቃጨርቅ ዘርፍ በፊዚካልና ኬሚካል የፍተሻ ወሰን የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ ሆኗል፡፡

በኢንስፔክሽን አክሪዲቴሽን ISO/IEC 17020፣ዘርፍ ደግሞ ኮንትሮል ዩኒየን ኢትዮጵያ ኢንስፔክሽን እና ሰርቲፍኬሽን ኃ.የተ.የግል ማህበርር በግብርና ምርቶች ኢንስፔክሽን፣ አፍሮ እስታር ኢንተርናሽናል ኮሜርሽያል ኤጀንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ኤ.ዋይ ኖብል ኢንስፔክሽን እና ሰርቪላንስ ሰርቪስ በግብርና ምርቶች ኢንስፔክሽን እና ናሙና አወሳሰድ የአክሬዲቴሸን ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በሰርቲፍኬሽን አክሪዲቴሽን ISO/IEC 17021 አሰርት ኢትዮጵያ ማኔጅመንት ሰርቲፍኬሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በማኔጅመንት ሲስትም ሰርቲፍኬሽን ዘርፍ አክሪዲት የሆኑ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ወደ አክሪዲቴሽን የመጣ የመጀመሪያው የግል ተቋም ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የፍተሻ ላቦራቶሪ እና የኢንስፔክሽን አክሪዲቴሽን ተቋማት የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ለውጭ ንግድ መቀላጠፍ የንግድ እንቅፋቶችን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆኑ በነዚህ ዘርፎች ወደ አክሪዲቴሽን ሊመጡ የሚገባቸው ተቋማት ወሰኖችን በማስፋትም ሆነ እስካሁን የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ ያልሆኑ ተቋማት ወደ አክሪዲቴሽን ሊመጡ ይገባል፡፡

በሕክምና ላቦራቶሪ ዘርፍ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት ሕብረተሰቡ በሚሰጡት የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት ላይ እምነት እንዲያሳድር ከማድረጋቸው በላይ ተደጋጋሚ ፍተሻን በማስቀረት ሕብረተሰቡ ለተጨማሪ ወጪ እንዳይዳረግ ያግዙታል፡፡

በኢንስፔክሽን ዘርፍ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡና ከሃገር የሚወጡ ምርቶች ትክክለኛ የኢንስፔክሽን ውጤት ይዘው እንዲወጡ በማድረግ ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ እነዚህ ተቋማት በሌሎችም ዘርፎች ማስፋት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በፍተሻ ላቦራቶሪ ዘርፍ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት ምርቶች በላቦራቶሪ ተፈትሸው የተቀመጠላቸው መስፈርቶች ማሟላታቸው የሚረጋገጥበት አንዱ መንገድ በመሆኑ ለምርት ጥራት መጠበቅ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ  የአክሪዲቴሸን ወሰኖቻቸውን በማስፋትና ያገኙትን አክሪዲቴሸን በማስጠበቅ ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል፡፡

ተቋሙ የአክሬዲቴሽን አገልግሎት የሚሰጣቸው በሕክምና ላቦራቶሪዎች ISO 15189  ለፍተሻ ላቦራቶሪዎች ISO/IEC 17025፣በኢንስፔክሽን ISO/IEC 17020 በፐርሰኔል ሰርቲፍኬሽን በISO/IEC 17024፣በምርት ሰርቲፍኬሽን ISO/IEC 17065፣የአመራር ስርዓት ሰርቲፍኬሽን ISO/IEC 17021 እንዲሁም በካሊብሬሸን ዘርፍ ISO/IEC 17025 ነው፡፡

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ለስድስት የሕክምና፣ ለሶስት የፍተሻ ላቦራቶሪዎች፣ ለሶስት የኢንስፔክሽን እና ለአንድ የሰርቲፍኬሽን ተቋም የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ሰጠ::