News

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ዛሬ የካቲት 14ቀን 2014ዓ.ም በአዲስ አበባ ውስጥ በጀመረው ስልጠና ከተለያዩ የመንግስትና የግል ሆስፒታሎች የተውጣጡ ከ20 በላይ የሕክምና ላቦራቶሪ ባለሙያዎችና የላቦራቶሪ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በስልጣናው ለሕክምና ላቦራቶሪዎች ISO 15189 ደረጃን መሰረት አደርጎ የሚሰጥ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዓላማም የሕክምና ተቋማት የአክሪዲቴሸን አገልግሎትትን ጠቀሜታ ተረድተው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው፡፡ተቋማቱ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ቢሆኑ ለሕብረተሰቡ ተአማኒነትና ብቃት ያለው አላቦራቶሪ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸው እንደሆነ በዚሁ ስልጠና ላይ የተገለጸ ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናውን ከተከታተሉ በኃላ ወደ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ ተቋሞቻቸውን ወደ አክሪዲቴሸን እንዲመጡ ለማገዝ ያስችላቸዋል፡፡በተመስሳይ ስልጠናው በፍተሻ ላቦራቶሪ ISO/IEC 17025 ከተለያዩ የመንግስትና የግል አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎች ለተውጣጡ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችና የጥራት ቁጥጥር የሥራ ሃላፊዎች ስልጠና እየተጠ ሲሆን ስልጠናው ተቋማቱ የሃገሪቱ ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችላቸው አቅም እንዲፈጥሩ የሚያስችላቸው በመሆኑ ሰልጣኞች ትኩረት እንዲሰጡትም ተጠይቋል፡፡በቀጣይ መሥሪያቤቱ ለሌሎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችና እንዲሁም የተለያዩ መንግስታዊያ መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ለመስጠት እቅድ የያዘ ሲሆን የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን በመላ ሃገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ ሕብረተሰቡና ተቋማት ስለ አክሪዲቴሸን ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል፡፡በሕክምናና ለፍተሻሻ ላቦራቶሪ ባለሙያዎችና ሃላፊዎች ለሁለት ቀን በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ከ35 በላይ የሥራ ሃላፊዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ለሕክምናና ለፍተሻ ላቦራቶሪዎች ስልጠና ሰጠየኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ከተለያዩ የመንግስትና የግል ሆስፒታሎችና የሕክምና ተቋማት እንዲሁም ኢንዱስትሪዎችና አምራች ድርጅቶች ለተውጣጡ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችና ሃላፊዎች ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡