News

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ለተስማሚነት ምዘና ተቋማት የሚሰጠውን የአክሪዲቴሽን  አገልግሎት የበለጠ ተደራሽ ለማድርግ በካሊብሬሽን ዘርፍ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ማድርግ እንደሚገባ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ተናገሩ

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አርአያ ፍስሃ ዛሬ ለፍተሻ ላቦራቶሪ አሰሰሮች ዓመታዊ  ኮንፍረንስ ሲጀመር እንደተናገሩት በፍተሻ ላቦራቶሪ መስክ የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን ለማስፋት ቅድሚያ የካሊብሬሸን ላቦራቶሪዎች ወደ አክሪዲቴሸን ሊመጡ ይገባል

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ለካሊብሬሸን ላቦራቶሪዎች ዓለም አቀፍ እውቅና ለመስጠት ዝግጅት ቢያደረግም አመልካች ባለመኖሩ አገልግሎቱን መስጠት አለመቻሉንና አገልግሎቱን ካልሰጠ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግምገማ እንዲደረግበት መጠየቅ ስለማይችል ከሌሎች የተስማሚነት ምዘና ዘርፎች ካሊብሬሸን ወደኃላ ቀርቷል ብለዋል

በሰርቲፍኬሸን ዘርፍ ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት ተቋሙ ዓlም አቀፍ ግምገማ እንደተካሔደበት አስታውሰው በሰርቲፍኬሸን  በግምገማ ወቅት የተገኙትን አነስተኛ ክፍተቶች ተቋሙ ማስተካከሉንና በቅርቡም ዓለም አቀፍ እውቅናው እንደሚገኝ ጠቁመዋል

የአሰሰሮች ዓመታዊ ኮንፍረንስ ዋና ዓላማ በዓመት ውስጥ የአሰስመንት ስራዎች ሲሰሩ በስራ ላይ ያጋጠሙ ክፍተቶችን በመገምገም በቀጣይ ክፍተቶቹን ለማስተካከል፣ በአሰሰሮች መካከል በአንድ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አረዳድ እንዲይዙ ማድረግና አዳዲስ የተለወጡ ሰነዶች ካሉ በነሱ ላይ ግንዛቤ ለመስጠት መሆኑንም ጠቁመዋል

የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን ለማስፋት የካሊብሬሽን ዘርፍን ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ማድርግ ያስፈልጋል ተባለ