News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት የፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት አዲስ አደረጃጀትን ተከትሎ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት የሚለው ስያሜ ወደ ኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት በመለወጡ የተቋሙን አዲስሎጎ አጸደቀ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ማኔጅመንት ዛሬ ጥር 9ቀን 2014ዓ.ም በአዳማ በጀመረው የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ የተወያየው በአገልግሎቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሸን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ተዘጋጀቶ የቀረበውን የተቋሙን አዲስ ሎጉ ሲሆን ሎጎው ተሰርቶ በቀረበው ደረጃ ጸድቋል፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ሎጎ በአለም አቀፍ ደረጃ መመዝገብ ስላለበት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት እንዲመዘገብ እንዲደረግ ማኔጅመንቱ ያጸደቀ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ስራዎቹ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው በመሆኑና ቀደም ሲል የነበረው የተቋሙ ሎጉ በዓለም አቀፍ ደረጃም የተመዘገበ በመሆኑ ሲቀየርም ለዓለም አቀፉ ተቋማት ማሳወቅ እንደሚገባ ተብራርቷል፡፡አዲሱ የተቋሙ ሎጉ በውስጥ አቅም በአቶ አዱኛ አብዲሳ -የአይሲቲ ዳይሬክተር እና በአቶ ታሪኩ ብርሃኑ -የቀድሞ የፅ/ቤቱ የአይቲ ባለሙያ መሰራቱ መንግስትንና ተቋሙን ከተጨማሪ ወጪ ማዳኑም በውይይቱ ወቅት የተነሳ ሲሆን የሎጉው ዝርዝር ትርጓሜም ከሎጎዉ ጋር በአቶ አዱኛ አብዲሳ ቀርቦ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡ ሎጎው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ እንደተመዘገበ ለተገልጋዮች እና ለህብረተሰቡ ይፋ ይደረጋል። የዚህ በተጨማሪ ማኔጅምንቱ አባላት የስድስት ወር የስራ አፈጻጻም ግምገማ ያካሔደ ሲሆን በዋና የስራ ሂደት በተለይ በአክሪዲቴሸን አገልግሎት ዘርፍ የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራትን ገምግሞ በቀጣይ ቅድሚያ ተሰጥቶ ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድርግ የአክሪዲቴሽን ጠያቂ ተቋማት በተፈለገው መጠን ማመልክት እንዳልቻሉ በሪፖርት የተጠቆመ ሲሆን ተቅማቱ ወደ አክሪዲቴሸን ባይመጡም ተቋሙ በባለሙያዎች ስልጠና፣የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣አዲሱን የተቋሙን ስያሜ ተከትሎ ሰነዶችን የማስተካከል ስራዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊሰሩ እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል፡፡ቀጣዮቹ ሶስት ወራት ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸማቸው ዝቅ ያሉ ተግባራትን ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ በስራ አፈጻጸም ግምገማው ወቅት የተነሳ ሲሆን የአክሪዲቴሸን አገልግሎት አክሪዲት ለሆኑ ተቋማት ትርጉም ባለው መልኩ ጠቀሜታ እንዲኖረው መስራት እንደሚያስፈልግም ተመልክቷል፡፡የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን የበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ተቋማት የበላይ አመራሮችን ስልጠና መስጠት አንዱ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ስራም ሊሆን ይገባል ተብሏል፡፡በተቋሙ የተያዙ ዋና ዋና እቅዶች በሶስተኛው ሩብ ዓመት ሊጠናቀቁ እንደሚገባ በማኔጅመንቱ ስምምነት ተደርሶበታል፡፡

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አዲሱን የተቋሙን ሎጎ አጸደቀ