ሰኔ 02፥2013 የአለም አክሬዲቴሽን ቀን በዓል #WAD2021የተስማሚነት ምዘና ተቋማት አክሪዲቴሸንን በአግባቡ ቢተገብሩ የሸቀጦችና የአገልግሎቶችን ዋጋ በመቀነስ ለኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ተናገሩ፡፡ የዓለም አክሪዲቴን ቀን በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ ተከበረ፡፡ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አርአያ ፍስሃ በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ ዛሬ የተከበረውን የዓለም አክሪዲቴሸን ቀን አስመልክተው እንደተናገሩት አክሪዲቴሸን ምርታማነትን በመጨመር፣አዳዲስ የገበያ መዳረሻ በመፍጠር፣የንግድ እንቅስቃሴውን በማቀላጠፍ ለኢኮኖሚው ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡አክሪዲቴሸን የጥራት መስፈርትን በማሟላት፣ ዋጋ ቆጣቢ በሆነ የምርት አቅርቦት እንዲኖር በማድርግ አምራች ድርጅቶችን አነቃቅቶ የሸማቹን ደህንነትና ጤና ብሎም የአካባቢ ድህንነትን ለማስጠበቅ ያስችላል፡፡ጽ/ቤቱ ባለፉት ዓመታት ከስርዓት ዝርጋታ፣ከሰው ሃይል ግንባታ፣ከግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በተጨማሪ በአክሪዲቴሸን አገልግሎት ለ56 የህክምና ደርጅትች በ83 የፍተሻ ወሰኖች እንዲሁም ለ34 ድርጅቶች ለፍተሻ ላቦራቶሪ በ39 የፍተሻ ወሰኖች የአክሪዲቴሽን አገልግሎት መስጠቱን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመው ከነዚህ ውስጥ 9 ድርጅቶች በሕክምና እንዲሁም 14 ደርጅቶች በፍተሻ አክሪዲቴሸናቸውን መነጠቃቸውን ገልጸዋል፡፡በኢንስፔክሽን ዘርፍም ለ9 ድርጅቶች በየ9 የፍተሻ ወሰኖች በሰርቲፍኬሽን ዘርፍ ለአንድ ድርጅት በአንድ የፍተሻ ወሰን የአክሪዲቴሸን አገልግሎት መሰጠቱን የተናገሩት አቶ አርአያ በኢንስፔከሽን ዘረፍ አንድ ድርጅት መነጠቁን ጠቁመዋል፡፡በዚህ ለግማሽ ቀን በተካሔደው ሴሚናር ላይ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌተንት ጽጌመላክ አክሪዲቴሽን የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ ከመደገፍ አንጻር ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ም/ዋና ዳይሬክተሩ በጽሁፋቸው የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ 17 ጎሎች እንዳሉትና እነዚህን ጎሎች ለማሳካትና ብልጽፅግናን ለማረጋገጥ ቅንጅትና አብሮ መስራት እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል፡፡ከየግብርና ሚኒስቴር የእጸዋት ጤናና ምርት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ሙላተ አባተ እንዲሁም ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የገቢና ወጪ እቃዎች ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክትሬት ከቅርንጫፎች ሃላፊ አቶ መለሰ በኩረስላሴ ፋይቶ ሳኒተሪ ሰርቲፍኬሸን የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ያለው ምን ተጽኖ እንዳለውና አክሪዲቴርሽን ከወጪና ገቢ እቃዎች አንጻር ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ጽ/ቤቱ በቀጣይ የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ በዲታል ስርዓት ለመጀመር ያከናወናቸውን ተግባራት የጽ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሩ አቶ አዱኛ አብዲሳ የተሳታፊዎቹ ያቀረቡ ሲሆን ጽ/ቤቱ አክሪዲቴሸንን ቀላልና ቀልጣፋ ለማደርግ ብዙ ርቀት መጓዙን አብራርተዋል፡፡ከዚህ በተጫመሪም የጽ/ቤቱን መለያዎች ብራንድ ማንዋል መዘጋጀቱን አቶ አዱኛ አንስተዋል በዚህ ለግማሽ ቀን በተካሔደው ሴሚናር ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል
የተስማሚነት ምዘና ተቋማት አክሪዲቴሽንን በአግባቡ ቢተገብሩ ለኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ- World Accreditation Day-2021