News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የሕክምና ላቦራቶሪዎች ወደ የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ ቢሆኑ ለሕብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት ይበልጥ ተአማኒነት ያገኛል ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተናገሩ፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጌተንት ጽጌመላክ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ለመንግስትና ለግል የሕክምና ተቋማት የላቦራቶሪ ኃላፊዎችና ባሙያዎችና በተዘጋጀው ስልጠና መክፈቻ ላይ እንደገለፁት የሕክምና ላቦራቶሪዎች ወደ አክሪዲቴሸን ለመምጣት ሊተገብሯቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል፡፡

ሕብረተሰቡ ከሕክምና ላባራቶሪዎች አስተማማኝ ውጤት ማግኘት ይፈልጋል ያሉ ምክትል ዋና ደይሬክተሩ ለዚህ አንዱ መንገድ የሕክምና ላቦራቶሪዎች ወደ የአክሪዲቴሸን ስርአት ዘርግተው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ነው ብለዋል፡፡

አክሪዲቴሸን ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት፣በቂ ሃብት ለመመደብ፣ ተደጋጋሚ ሥራዎችን ለማስቀረት፣ የሚፈጠሩ ስህተቶችን ለመቀነስ፣በደንበኞች ዘንድ እምነት ለማሳደር እና በግሉ ዘርፍ ገቢን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት ተቋማት የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ለማግኘት በውጭ ምንዛሪ ከፍለው ከውጭ ሃገር የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ የሚሆኑ ተቋማት እንደነበሩ ያስታወሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በአሁኑ ወቅት ግን በተመጣኝ ዋጋ አገልግሎት በሃገር ውስጥ እየተሰጠ በመሆኑ ተቋማት ይህን አገልግሎት ሊጠቀሙ ይገባል ብለዋል፡፡

ጽ/ቤቱ ተቋማት ወደ አክሪዲቴሸን እንዲመጡ ተገቢውን መረጃ የማዳረስ ሥራ እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ጌተንት በዚህ መረጃ ተጠቅመው ወደ አክሪዲቴሸን የሚመጡ የህክምና ላቦራቶሪዎች ቢኖሩም የላብራቶሪ አገልግሎት እየሰጡ ካሉ ተቋማት ብዛት አንጻር ወደ አክሪዲቴሸን እየመጡ ያሉት ጥቂት መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ስልጠናው በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን የሕክምና ላቦራቶሪዎች የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ለመሆን ሊተገብሯቸው በሚገቡ ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ይቀጥላል፡፡

(14) Facebook

የሕክምና ላቦራቶሪዎች ወደ አክሪዲቴሽን ቢመጡ አገልግሎታቸው ይበልጥ ተአማኒነት ያገኛል