News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ሜኔጅመንትና የቴክኒክ ቡድን አባላት በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት አደረጉ፡፡

የጽ/ቤቱ የሜኔጅመንትና ዬክኒክ ቡድን አባላት በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት ያደረጉበት ዋና  ዓላማ በፓርኩ ያሉ ኢንዱስትሪዎችን በመለየት ላቦራቶሪ ያላቸውን፣ የኢንስፔከሽንና  የሰርቲፍኬሽን ዘርፉን በመለየት በጽ/ቤቱ በኩል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ይግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ወደ አክሪዲቴሽን እንዲመጡ ለማድርግ ነው፡፡

በኢንዲስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ የማምረቻና የተለየዩ ተቋማት ላቦራቶሪ ያላቸው ላቦራቶሪዎቻቸውን ወደ አክሪዲቴሸን ለማምጣት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤተ ዋና ዳይሬክተር በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አርአያ ፍስሃ የጽ/ቤቱ የማኔጅመንትና የቴክኒክ ቡድን አባላት በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመገኘት ባደረጉት ጉብኝት ላይ እንደተናሩት በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ አምራች ድርጅቶች ለአክሪዲቴሸን አገልግሎት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት ከተደረገባቸው ተቋማት መካከል የኤስ.ጂ.ኤስ ኩባንያን የተመለከቱ ሲሆን ተቋሙ በኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት በ14 የፍተሻ ወሰኖች የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን እንደ መልካም ውጤት ተመልክተው ነገር ግን የቴክስታይል ዘርፉ ከ72 የማያንሱ የፍተሻ ወሰኖች ያሉት በመሆኑ ድርጅቱ የአክሪዲቴሸን ወሰኑን ሊያሰፋ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የኤስ.ጂ.ኤስ ኩባንያ እየሰራቸው ያሉት ተግባራት የሚያበረታቱ መሆናቸውን አቶ አርአያ ጠቁመው ከዚህ የበለጠ ለመስራት ጥረት ማድርግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ ጄ፡ፒ የቴክስታይል ኩባንያን የጽ/ቤቱ ማኔጅመንትና የቴክኒክ ቡድን አባላት የጎበኙ ሲሆን የጉብኝቱ ዓላማ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ ላቦራቶሪዎች መን ዓይነት የፍትሻ መሳሪያ አላቸው፣የን አይነት የፍተሻ ወሰን አገልግሎት ይሰጣሉ፣ከማነ ጋር ተጣምረው መስራተ ይችላሉ የሚሉትን ነገሮች ለይቶ ድጋፍ ለማድርግ እንደሆነም ተብራርታ፡፡

በተመሳሳይ በኢንዱስትሪ ፓርኩ የጂንስ ሱሪዎችን አመራች የሆነውን ኩባንያ የጉብኝቱ አካል የሆነ ሲሆን ኩባንያው ለውጭ ገበያ እያመረታቸው ያሉ ምርቶች በአክሪዲቴሽን ቢደገፍ ወደ ዓለም ገበያ ለመግባት ቀላል መንገድ እንደሆነ በጉብኝቱ ላይ የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ለኩባንያው ሃላፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡

የጽ/ቤቱ ማኔጅመንትና የቴክኒክ ቡድን አባላት የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርከን ጎበኙ አደረጉ