News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና ለሲዳማ ክልል የተለየያ ቢሮዎች ጽ/ቤቱ በአክሪዲቴሸን ዘርፍ እየሰጣቸው ያሉትን አገልግሎቶች አውቀው እንዲገለገሉ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን ታህሳሰ 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሃዋሳ የተሰጠ ሲሆን ታህሳስ 22 ቀን 2013ዓ.ም የደቡብ ብሔር ሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የተሰጠውን ስልጠና የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ የሰጡ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማ  በደቡብ ብሔር ብሔር ብሔረሰቦች  ክልል የሚገኙ የተለያዩ ቢሮዎች የአክሪዲቴሽን ጽ/ቤ የሚሰጣቸውን የአክሪዲቴሽን አገልግሎቶች አውቀው ወደ አክሪዲቴሽን እንዲመጡ  መረጃ ለመስጠት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አክሪዲቴሸን ዓለም አቀፍ ተወዳሪነትን ለማሳደግ አንዱ መንገድ እንደሆነ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚገኙ የተለያዩ ላቦራቶሪዎች፣ ፣የኢንስፔክሽንና የሰርቲፍኬሸን ተቋማት የአክሪዲቴሸንን ጥቅም ተረድተው ወደ አክሪዲቴሸን ለመምጣት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ጽ/ቤቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን ለክልሉ ቢሮ ሃላፊዎችና ምክትል ሃላፊዎች ሲያዘጋጅ ዋና ዓላማው ሃፊዎች የአክሪዲቴሸንን ጥቅም ተረድተው ወደ አክሪዲቴሽን ሊመጡ የሚገባቸው ተቋማት ወደ ለአክሪዲቴኸን እንዲበቁ ድጋፍ እንዲያደረጉ መሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ታህሳስ 23 ቀን 2012ዓ.ም የተሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሲዳማ ክልል የሰጡት ደግሞ የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌተንት ጽጌመላከ ሲሆኑ ስልጠናው ክልልሉ አዲስ በመሆኑ የአክሪዲቴሸን አገለግሎትን ጠቀሜታ አውቆ እንዲሰራ መረጃ ለመስጠትና መሰረት ለመጣል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ጽ/ቤቱ ስልጠናውን በክልሉ የቢሮ ሃላፊዎችና ምክትል ሃላፊዎች ደረጃ እንዲሰጥ መዘጋጀቱን የተናገሩት አቶ ጌተንት ክልልሉ ለአክሪዲቴሸን ትኩረት ሰጥቶ ከጽ/ቤቱ ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ቢሮው ለግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን የተናሩት ምክትል ዋና ዳይሬከተሩ የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት በመሆኑና ብዙ ላቦራቶሪዎችና የኢንስፔከሽን ስራዎች ስላሉ አክሪዲቴሽን የውጭ ንግዱን ማቀላጠፍ አንዱ መንገድ በመሆኑ ክልልሉ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት ይግባል ሲሉም ተናግርዋል፡፡

ጽ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ አክሪዲቴሸንን በተመለከተ ክልልሉን በተለይም በስልጠና ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይ የተጠናከረና ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ለማዘጋጀትም ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ጽ/ቤቱ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና ለሲዳማ ክልል የተለየያ ቢሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ