News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች እና ለሠራተኞቹ በውጤት ተኮር እቅድ ዝግጅት፣በተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ እና በፌደራል መንግስት የሰራተኞች አዋጅ 1064/2010 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ከታሕሳስ 08 እስከ ታሕሳስ 09 ቀን 2015ዓ.ም ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ በተካሄደው ስልጠና ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ባስተላለፉት መልዕክት ተሳታፊዎች ስልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡

የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት ላይ ስልጠናውን የሰጡት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ብዙዓለም እንዲሁም የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ስርዓትን የተመከለተ ገለጻ ያቀረቡት የኮሚሽኑ የሲስተም አናሊስት ባለሙያ አቶ ደሱ ጋሹ ሲሆኑ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ 1064/2010 በተመለከተ የአገልግሎቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ውብታየሁ ባቲ ሰፋ ያለ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የአገልግሎቱን አዲሱን አደረጃጀት፣ተልዕኮ፣ራዕይን ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኞች መብትና ግዴታዎች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ላይ ገለጻ በማድረግ ሁሉም ሰራተኞች አዋጁ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርገዋል ፡፡

በመጨረሻም የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ በተሰጡት ስልጠናዎች ላይ ሁሉ ግንዛቤ ኖሮት ለአገልግሎቱ ተልዕኮ መሳካት ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አክለውም በውጤት ተኮር ምዘና ላይ ሰራተኞች በሰሩት ሥራ ብቻ መመዘን እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው 62 ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ
አክሬዲቴሽን አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች
የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አቶ መላኩ ብዙዓለም
የአገልግሎቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ውብታየሁ ባቲ
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ከታሀሳስ 7-8 2015 ዓ.ም በአዳማ እየተሰጠ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ::