የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አጠቃላይ የአሰሰር ካሊብሬሽን ስልጠና አካሄደ
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አጠቃላይ የአሰሰር ካሊብሬሽን ስልጠና በአመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን 6 September 2022ዓ.ም አሰሰሮች፤ የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት የ proficiency Test policy, Traceability policy, Traceability Checklist, Timeline rule, Use of ILAC/IAF mark and Use of EAS symbol ላይ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄች ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ እንደገለጹት የሚሰጠው አገልግሎት ተደራሽና ቴክኖሎጂን የሚከተል እንደሚሆን ጠቁመው በመጪው ግንቦት 2023ዓ.ም ለሚደረገው አለም አቀፍ ግምገማ ሁሉም የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት እና የሀገር ገጽ ግንባታ በመሆኑ ለሚጨመሩ አዳዲስ ወሰኖች ላይ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አጠቃላይ የአሰሰር ካሊብሬሽን ስልጠና አካሄደ