News

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት የሴቶችን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችላቸውን የሴቶች ፎረም መሰረቱ፡፡

የአገልግሎቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ባለሙያ ወ/ሮ አዜብ ሰለሞን ጥር 20 እና 21ቀን 2014ዓ.ም የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ባደረጉት ስብሰባ የአገልግሎቱ የሴቶች ፎረም መመስረቱን መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ፎረሙ በዋናነት ሴቶች በተቋሙ ውስጥ ያላቸውን ማህብራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግ የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሴት አመራሮችን ለመፍጠር የፎረሙ መመስረት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ወ/ሮ አዜብ ጠቁመው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሴቶችንም በአቅም በመገንባትና ራሳቸውን በትምህርት እንዲያሳድጉ በማገድ የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድርስ ፎረሙ ጠንክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አክሪዲቴንሽ አገልግሎት የሴቶች ፎረም ተመሰረተ