News

አዲስ አበባ፣ 20/05/2014(ንቀትሚ) በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የብሔራዊ ጥራት መሠረተ ልማት ፕሮጀክትን ተግባራዊ የሚያደርጉ የስራ ክፍሎች እና ተጠሪ ተቋማት የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፡፡የግምገማ መድረኩ ዋና ዓላማ የጥራት መሠረተ ልማት ፕሮግራምን ተግባራዊ በሚያደርጉ የስራ ክፍሎችና ተቋማት እንዲሁም የብሄራዊ የጥራት መሠረተ ልማት ፐሮጀክት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም መገምገም እና የቀጣይ ስድስት ወራት ዕቅድ ክለሳ ላይ ወይይት ማድረግ መሆኑን የጠቆሙት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሰረተ ልማትና ማረጋገጫ ሚ/ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ውይይቱ በቀጣይ ለሚኖረው አፈጻጸም አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጥራት መሠረት ልማት ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የስራ ክፍሎችና ተጠሪነታቸው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሆኑ ተቋማት ያለፉት ስድስት ወራት የመደበኛ ስራዎች አፈጻጻምና ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የተሰሩ ስራዎች ላይ ያተኮረ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

Source:ንቀትሚ

የብሔራዊ ጥራት መሠረተ ልማት ፕሮግራም የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ