የኢትዩጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን /March 8 / ምክንያት በማድርግ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘውን የተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካነሰር ድርጅት ህፃናትን ጎበኙ፡፡
የጽ/ቤቱ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ባለሙያ ወ/ሮ አዜብ ሰለሞን አስተባሪነት የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ህጻናቱን ዛሬ የካቲት 24ቀን 2013ዓ.ም የጎበኙ ሲሆን የጉብኝቱ አላማም ህጻናቱ ያሉበትን ሁኔታ በመመልከት ሰራተኛውን በማስተባበር ድጋፍ ማድርግ የሚቻልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው፡፡
ሠራተኞቹ በጉብኝታቸው ለለጽዳት አገልግሎት የሚሆን ሶፍት፣ሳኒታይዘርና ፈሳሽ ሳሙና እና ከሰራተኛ የተሰበሰቡ አልባሳት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም ለህጻናቱ አቅም የፈቀደውን ድጋፈ ለማድርግ እነደሚበራ ባለሙያዋ ተናገርዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ባለፈው አመት በተመሳይ ህጻናቱን ጉብኝት ያደረጉና ድጋፍም የሰጡ ሲሆን ድርጅቱ በአሁኑ ወቅውት ህጻናቱን በተሻለ ሁኔታ ላይ እንዲገኙ ለማድርግ የሰራቸው ተግባራተ እንዳስደሰታቸው ተናገርዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ሠራተኞች የካነሰር ድርጅት ህፃናትን ጎበኙ፡