የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን ተደራሽ ለማድርግ የፍተሻ ላቦራቶሪ ያላቸውና ወደ አክሪዲቴሸን ሊመጡ ይችላሉ ላላቸው ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣቱ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ እይሰጠ ነው፡፡
ጽ/ቤቱ ዛሬ በቢሸፍቱ ከተማ የጀመረው ስልጠና በISO/IEC 17025 በፍተሻ ላቦራቶ አክሪዲቴሸን ዘርፍ ያተኮረ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በነገው እለትም ይቀጥላል፡፡
በስልጠናው ላይ ከአዲስ አበባ ዩነቢቨርስቲ የደብረዘይት እንስሳት ህክምና ኮሌጅ፣ከብሔራወ የእንስሳት ሕክምና ላቦራቶሪን ጨምሮ ከተለያ ተቋማት የተውጣጡ 25 ተሳታዎች ተካፋይ የሆኑ ሲሆን ስልጠናው የአክሪዲቴሸኸን አገልግለኮት ተጠቃሚ ለመሆን ተቋማት ሊያሟሉ ስለሚገባቸው መስፈርቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ተቋማት ከሰነድ ዝግጅት ጀምሮ የአሰራር ስርአት ሊዘረጉ እንደሚገባ የፍተሻ አክሪዲቴሽን ቡድን መሪ ወ/ሮ መሰይ መገቹ በስልጠናው ላይ የገለፁ ሲሆን ጽ/ቤቱ ተቋማት ወደ አክሪዲቴሸን እንዲመጡ መሰረታዊ የግነዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡
ተቋማት ይህም መሰረት በማድርግ ራሳቸውን ወደ ዓለም አቀፍ እውቅና ለማምጣት ሊሰሩ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ጽ/ቤቱ በተመሳሳይ ታህሳስ 22 ቀን 2013ዓ.ም በሃዋሳ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የተለየዩ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ለሲዳማ ክልል የተለየዩ ቢሮ ኃላፊዎች ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፡፡