የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት የኮቪድ 19 ወረርሺኝ በተከሰተበት ወቅት የጽ/ቤቱን ሥራ በኦን ላይን ለማድረግና አዳስ የአክሪዲቴሸን ወሰኖችን ለማስፋት ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ገለጹ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩአቶ አርአያ ፍስሃ የጽ/ቤቱን የ2013 ዓ.ም የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ከሰራተኞች ጋር በጋራ በተካሔደበት ወቅት እንደተናገሩት የኮቪድ ወረርሺኝ የአክሪዲቴሽን አገልግሎት በታቀደው መሰረት ለማስኬድ በሃገርም ሆነ በአገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈተና ቢሆንም ጽ/ቤቱ ወቅቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የኦን ላይን አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችለውን ሥራ በመስራተ ሥራውን ወደ ማጠናቀቅ እየረሰ ነው፡፡
ጽ/ቤቱ የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን በኦን ላይን ለመስጠት በዓለም ባንክ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሥራ እየሰራ እንደሆነ የተናሩት ዋና ዳይሬክተሩ ሥራው ሲጠናቀቅ በየደረጃው ያለውን ሰራተኛ በማሰልጠን፣ የትርፍ ጊዜ አሰሰሮችን በተለያ ቡድን በመክፈል ሥልጠና በመስጠት ወደ ተግባር ይገባል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከአሁን ቀደም ጽ/ቤቱ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላገኘባቸውን የአክሬዲቴሸን ወሰኖች በማስፋት በሰርቲፍኬሸን ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት ማመልከቻ መግባቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ በሰነድ ዝግጅት በኩልም ከ60 በላይ አዳዲስ ሰነዶች እንዲሁም 23 የተከለሱ ሰነዶች መዘጋጀታቸውንና በዓለም ባንክ ፕሮጀክት በውጭ አማካሪዎች ተዘጋጅቶ የተላከው ሰነድ በጽ/ቤቱ እንደ አዲስ መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡
የሰነድ ዝግጅቱ ከፍተኛ ድካም እንደጠየቀ የተናገሩት የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌተንት ጽጌመላክ ኮር ፎከስ የተባለው ድርጅት በሰነድ ዝግጅት እንዲያካሂድ ለጽ/ቤቱ የተመረጠ ቢሆንም ጽ/ቤቱ ሰነዶቹን እንደ አዲስ እነደሰራቸው ተናግርዋል፡፡
ጽ/ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት በተለያ ዘርፎች በርካታ ተግባራተን ማከናወኑን የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የኮቪድ መከሰት በአክሪዲቴሸኑ እንቅስቃሴ ላይ ተጽኖ ማሳደሩንም ገልጸዋል፡፡
ይህም ሆኖ ሥራው አለመቋረጡንና በኮቪድ ወቅትም የአክሪዲቴሸን አገልግሎት መሰጠቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ይሁን እንጂ በእቅድ ሊከናወኑ ይገባቸው የነበሩ የክትትል ግምገማዎች ወቅታቸውን ጠብቀው መካሔዳቸውን አቶ ጌትነት ጠቁመው አክሪዲቴሸን አገልግሎትም የዓለም አቀፍ አሰራሩን ተከትሎ መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ የኮቪድ ወረርሺኝን ከግንዛቤ ባስገባ ሥራዎች በተቻለ በእቅዳቸው መሰረት እንዲፈፀሙ ሁሉም ሰራተኛ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ጽ/ቤቱ ከሥራ አፈፃፀሙ በተጨማሪ በሃገራችን ለ16ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17 ጊዜ የተከበረውን የጸረ ሙስና ቀንንም ያከበረ ሲሆን በሥነ ምግባር የታነጸና ሙስናን የሚጸየፍ ሠራተኛ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚችል በመድርኩ ላይ ተገልጿል፡፡
የጽ/ቤቱ የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክትሬተ ዳይሬክተር ወ/ሮ ጌጡ መንጀክሶ እለቱን አስመልክተው ባቀረቡት ጽሁፍ የመንግስት ሰራተኛው መንግስት የሚያወጣቸውን ሕጎችና መመሪያዎች በማክበር ሙስናን በመጠየፍ ለሃገሩ እድገት የበኩሉን አስታዋጽኦ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
መንግስት ሁሉ ተሿሚና የመንግስት ሠራተኛ ሃብት ማስመዝገብ እንዳለበት ያወጣውን መመሪያ ሁሉም ሰራተኛ ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሚገባ የተናገሩት ዳይሬክተርዋ ሠራተኛው ማንኛውንም አገልግሎት ሲሰጥ በቀናነት፣ከአድሎና ከእጅ መንሻ በፀዳ በልኩ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ጽ/ቤቱ የኦን ላይ አገልግሎትን ለመጀመር ያከናወናቸው የግባራት በጽ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር አቶ አዱኛ አብዲሳ የቀረበ ሲሆን ተቋሙ ወደ ኦን ላይን አገልግሎት ሲገባ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ ተቋማት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
በርካታ አገልግሎቶች ወደ ኦን ላይ እየመጡ እንደሆኑ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ጽ/ቤቱን ራሱን ከዘመኑ ጋር እንዲሔድ ማድረጉ የሚጠበቅ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡