News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድርግ አክሪዲት የሆኑ ተቋማትን በአክሪዲቴሽኑ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባል ተባለ፡፡

የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድርግ አክሪዲት የሆኑ ተቋማትን በአክሪዲቴሽኑ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ሲሉ የኢዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት የሕዝብ ክንፍ አባላት ተናገሩ፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት ዛሬ በአዲስ አበባ ከጽ/ቤቱ የሕዝብ ክንፍ አባላት ጋር በጽ/ቤቱ የ2012 ዓ.ም የሥራ አፈፃፃምና የቀጣዮቹን አስር ዓመታት እቅድ አስመልክቶ ባሔደው የጋራ የውይይት መድረክ ተሳታፊዎቹ እንዳሉት አክሪዲቴሽን በሃገሪቱ ምርቶችና አገልግሎቶች ጥራት እንዲጨምር በማደርግ ከፍተኛ ድርሻአለው፡፡ተቋማት ወደ አክሪዲቴሽን እንዲመጡ አስፈጻሚ አካላት አክሪዲት የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት የሚለዩበት መስፈርት ሊኖራቸው ይገባል ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች በአሁኑ ወቅት በርካታ ተቋማናት ወደ አክሪዲቴሽን ሊመጡ ሲገባቸው ወደ አገልግሎቱ እየመጡ አይደለም፡፡ለዚህ አንዱ ምክንያት አክሪዲት በሆኑና ባልሆኑ ተቋማት መካከል ልዩነት አለመኖሩ ነው ያሉት የስብሰባው ተሳታፈዎች በሕክም፣በፍተሻ ላቦራቶሪ፣ እንዲሁም በኢንስፔክሽንና ሰርቲፍኬሽን ዘርፍ የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት የበለጠ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርአት ሊፈለግ ይገባል ብለዋል፡፡ጽ/ቤቱ እቅዱን አዘጋጀቶ ለሕዝብ ክንፍ አባላት ለአስተያየት ማቅረቡ ጥሩ መሆኑን የጠቆሙት የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣይ የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችና የዘርፉ ተከታታይ ስልጠናዎች ሊሰጡ ይገባል ብለዋል፡፡የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ጽጌመላክ ጽ/ቤቱ በአክሪዲቴሽን አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድግ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ይበልጥ ተፈላጊ የሚሆንበትን ሥርአት ለመዘርጋትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ጽ/ቤቱ በሁሉም ዘርፎች የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን ለመስጠት ሰነዶች በማዘጋጀት፡ባለሙያዎችን በማብቃትና ተገቢውን የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ራሱን ብቁ አድርጎ እየጠበቀ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጌትነት ሆኖም ተቋማት በሚፈለገው መጠን ወደ አክሪዲቴሽን አገልግሎት እየመጡ አይደለም ብለዋል፡፡ጽ/ቤቱ በግንዛቤ ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለመፍታት እንደሚሰራ ጠቁመው ነገር ግን አገልግሎቱ አስገዳጅ ባለሙሆኑ በርካታ ተቋማት ወደ አክሪዲቴሸን ለመምጣት ያላቸው ፍላጎች የጎላ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡ለነዚህ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባና ጽ/ቤቱም ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ጥራት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድርግ አክሪዲት የሆኑ ተቋማትን በአክሪዲቴሽኑ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባል ተባለ፡፡