News

መጋቢት 01 ቀን 2015ዓ.ም

‘’ዓለማችን ያለሴቶች ዋጋም ውበትም የላትም’’

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓልን በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት መሰብሰቢያ አዳራሽ አከበሩ።

ዓለም ያለሴቶች ዋጋም ውበትም የላትም ሲሉ በዓሉ ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ ሴቶችን ማብቃት የስልጣኔ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።ሴቶችን ማብቃት ቤተሰብን፣ጎረቤትን እንዲሁም በአጠቃላይ ህብረተሰብን ማብቃት መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ መሰረት አገራችን አሁን ካለችበት የከፋ ድህነት ማላቀቅ የሚቻለው የሴቶችን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አቅም ማሳደግ ስንችል መሆኑን ተናግረዋል።

አብዛኞቹ የኢትዮጵያ እናቶች በትልቅ መስዋዕትነት ለዚህ ያበቁን መሆኑን ጠቅሰው ለሴቶች ያላቸው ክብር ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ ህህህከሴቶች ጎን በመቆም የሰለጠነ ማህበረሰብ መፍጠር እንዳለብን በማሳሰብ መልካም የሴቶች ቀን በዓል እንዲሆን ለተሳታፊዎች ተመኝተዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የአንዴ ማማ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ መቅደስ ተሾመ የድርጅቱ ፕሮጀክት የሆነው “የእናት መንፈስ ፍቅር ፕሮጀክት” ዓላማ ሴት የህብረተሰብ ክፍሎችን የማብቃትና የአካባቢን የብክለት የመጠበቅ ስራዎች ላይ ገለጻ አቅርበዋል።የወደቁ ወረቀቶችን በመሰብሰብ እና መልሶ ስራ ላይ በማዋል በርካታ እናቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በገለጻው አብራርተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና  ዳይሬክተር መሰረት በቀለ(ዶ/ር) ለአንዴ ማማ ድርጅት ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ ለድርጅቱ ድጋፍ ለማድረግ በኢንስቲትዩቱ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ ድርጅቱ ለሚያከናውናቸው ስራዎች ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ አገልግሎቱ የወደቁ ወረቀቶችን በመሰብሰብ ለድርጅቱ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ድርጅቱ የሚያመርታቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት ድጋፍ እንደሚያደርጉ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማተ ናግረዋል።

ከሴቶች መብት ጋር ተይይዞ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 35 ላይ የተደነገጉ መብቶች ላይ በአገልግሎቱ የህ ግባለሙያ በአቶ መሀመድ አረቡ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።በመጨረሻም ለአገራችን ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሴቶች እና የሰሩዋቸው ገድሎች ላይ በአገልግሎቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቡድን መሪ በወ/ሮ አዜብ ሰለሞን ገለጻ ቀርቦ ውይይት በማድረግ በዓሉ ተጠናቋል።

በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ እንዲሁም በአገራችን ለ47 ጊዜ’’ እኔ የእህቴ ጠባቂነኝ’’ በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

የአገልግሎቱ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች የዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን በዓልን አከበሩ