News
በክብርት ወ/ሮ አይሻ ያህያ የተመራው በኢፌዲሪ ህዝብ ተወካየች ምክርቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ/ም በኢትዮጵያ አክሪድቴሽን አገልግሎት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ጎብኝተዋል፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎትን በጎበኙብት ወቅት የሚሰጣቸውን የአክሬዲቴሽን አገልገሎት ማለትም በፍትሻ ላብራቶሪ፣በህክምና ላብራቶሪ፣ በኢንስፔክሽን እና ሲስተም ሰርትፍኬሽን የአለም አቀፍ እውቅና ያገኘባቸው ሲሆን ለኢኮኖሚ እድገት ለህብረተሰብ እና አካባቢያዊ ደህንነት ላይ ያለውን ጉልህ ድርሻ በአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ ወሰኖችን የማስፋት ስራ እንድሚስራ እንዲሁም የተቀናጀ ስራ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር እና ከጥራት መሰረተ ልማት ጋር መኖሩን ገልጸው በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም የተስማሚነት ምዘና አካላትየአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠቅሰዋል።በመቀጠልም ከቋሚ ኮሚቴ አባላት የሚያስፈልጉ ድጋፎች እና በተንሱ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ዋና ዳይሬክተሯ ሰተውበታል።
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ አክሪድቴሽን አገልግሎት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ጎበኙ፡