News

ሕብረተሰቡ ቅሬታ ከሚያነሳባቸው የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ የጤና አገልግህሎቱ በመሆኑ የጤና አገልግሎቱን ማዘመንና የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ ማድርግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሊሆን ይግባል ሲሉ የኦሮሚያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን  የሳይንስ ዘፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገለፁ

የባለስልጣኑ የሳይንስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ልጃለም ረጋሳ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት በአዳማ የሕክምና ላቦራቶሪ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት አክሪዲቴሽን በሕክምና ዘርፍ አስተማማኝ ውጤት ለማግኘት አንዱ መንገድ ነው

መንግስት እንደሃገር ለጥራት መሰረተ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እደሆነ የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይረክተሩ የኦሮሚያ ክልልም በተለያዩ ዘርፎች ከሕብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት በርካታ ትግባራት እየሰራ እንደሆነ ጠቁመው በጤና አገልግሎቱ ዘርፍም አንዱ የአገልግሎት እርካታ ያለተገኘበት በመሆኑ ትኩረት ይሰራል ብለዋል

ይህንን ዘርፍ ለማዘመንና ለማሳደግ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ዶክተር ልጃለም ጠቁመው የኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ጋር ተቀራርቦ እየሰራ መሆኑንና በክልል የሚገኙ የመንግስትም ሆነ የግል የህክምና ተቋማት ስለ አክሪዲቴሸን መረጃው ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል

የስልጠናው ዋና ዓላማ ከሃገር አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በክልሉ የሕክምና አገልግሎት ጥራትን ማሳደግ መሆኑንና ይህም ዓላማ እንዲሳካ የሁሉም ባለሙያ አስተዋጽኦ እንዲሚያስፈልግ ተናገረዋል

መረጃው ካለና በአግባቡ ግንዛቤ ከተያዘበት በቀጣይ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ለመሆን መንገዱ ይከፈታል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ሰልጣኞች ደረጃውን በአግበቡ ተረድተው ወደ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ ምን ሊሰሩ እንደሚገባ በማሰብ ለውጥ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አሳስቸበዋል

ስልጠናው ከሰዓት በኃላ በቡድን ውይይት የቀጠለ ሲሆን በነገው እለትም በተመሰሳይ ከሰአት በፊት በደረጃው ላይ ስልጠና ከተሰጠ በኃላ ከሰአት በኃላ የቡድን ውይይት ይኖራል

የጤና ተቋማትን የአክሬዲቴሸን ተጠቃሚ ማድርግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል