የኢትዮያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት በISO/IEC17020 የዓለም አቀፍ ደረጃ መሰረት አደርገው የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ለሆኑ የኢንስፔክሽን ተቋማት ስልጠ ሰጠ፡፡
ጽ/ቤቱ ስልጠናውን ያዘጋጀው ጽ/ቤቱ የዓለም አቀፉ የላቦራቶሪዎች አክሪዲቴሸን ትብብር ፈራሚ ሙሉ አባል በመሆኑና የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ የኢንስፔክሽን ተቋማትን የአክሪዲቴሽን ሲምቦል የሚጠቀሙ በመሆኑ በሲምቦል አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው፡፡
የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክትር አቶ ጌትነት ጽጌመላክ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የአክሪዲቴሽን ተጠቃሚ የሆኑ የኢንስፔክሽን ተቋማት የሚያወጧቸው የኢንስፔክሽን ሪፖርቶች የጽ/ቤቱን ሲምቦል የሚጠቀሙ በመሆኑ ሲምቦል ሲጠቀሙ ዓለም አቀፍ ህግን ሊከተሉ ይገባል፡፡
ጽ/ቤቱ ተቋማት ህጎችን አክብረው ሥራቸውን እንዲሰሩ ስልጠናው መዘጋጀቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመው ስልጠናው በኮቪድ ወቅት ጽ/ቤቱ የተለያ ሰነዶችን የከለሰ በመሆኑ በተከለሱ ሰነዶችም ላይ ተቋማቱ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የኢንስፔክሽን አክሪዲቴሽን አገልግሎት የጊዜ ሰሌዳንም በተመለከተ ቀደም ሲል የነበረው የሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ወደ አራት አመት ተኩል በመለወጡ ይህንንም የኢንስፔክሽን ተቋማቱ እንዲያውቁት እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡
ሌላው ኮቪድ በተስፋፈበትና አብዛኛው የሥራ እንቅስቃሴ በተዘጋበት ወቅት የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን በኦፍሳይት አሰስመንት ለመተግበር የተደረገው ጥረትና የገጠሙ ችግሮችንም በተመለከተ በስልጠናው ተካቷል፡፡