News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት በኮንስትራክሽንንና በብረታብረት ዘርፍ ለተሰማሩ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪዎች የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ፡፡

ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ለኮንስትራክሽንንና በብረታብረት የማምረቻ ተቋማትና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መክፈቻ ላይ የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ጽጌመላክ ባደረጉት ንግግር ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚያቀርቡት ምርት ጥራን የጠበቀ እንዲሆን አንዱ መንገድ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ መሆን ነው፡፡

እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ የኮንስትራክሽን ዘርፉ በሃገሪቱ በፍጥነት እያደገ ያለ ዘርፍ በመሆኑ የኮንስትራክሽን ግብአት የሚያቀርቡ ተቋማት ለምርት ፍተሻ የሚጠቀሙባቸው ላቦራቶሪዎቻቸው ወደ አክሪዲቴሽን ቢመጡ የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በዝርዝር ያቀረቡት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የግንዛቤ ስልጠናው በዋናነት ተቋማት ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አውቀው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡት የጽ/ቤቱ የኢንስፔክሽን አክሪዲቴሸን ባለሙያ አቶ ዘውዱ ገብረሚካኤል ተቋማት ምርቶቻቸው ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት ጥራቱን የጠበቀ ለማድርግ አንዱ መንገድ አክሪዲት የሆኑ የኢንስፔክሽን ተቋማትን መጠቀም አልያም ላቦራቶሪዎቻቸውን  አክሪዲት ማስደረግ የኢንስፔክሽን ስርአታቸውን ማጠናከር፣ አክሪዲት በሆኑ ላቦራቶሪዎች መጠቀም ነው ብለዋል፡፡

አክሪዲቴሸን የአጭር ጊዜ ሥራ እንዳልሆነ የተናገሩት አቶ ዘውዱ ተቋማት የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ለመሆን ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል፡፡ አክሪዲቴሽን ለደንበኞች እምነት ይሰጣል፣ምርትና አገልግሎቶች ተወዳዳሪ እነዲሆኑ ያደርጋል ሲሉም ተናግርዋል፡፡

ጽ/ቤቱ ለተለየያ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ