የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጌትነት ጽጌመላክ እንዲሁም የጽ/ቤቱ የማኔጀመንት አባላት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በተካሔደው የችግኝ ተከላ ላይ ተሳተፉ፡፡ዋና ዳይሬክተሩና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንዲሁም የማኔጅመንቱ አባላት ሰኔ 22 ቀን 2012ዓ.ም በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጀው በአረንጓዴ አራሻን የማሳረፍ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል፡፡የሚኒስቴር መሥሪያቤቱ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ለበላይና ለመካከለኛ አመራሩ 2 ሺህ ችግኞች እንዲተከሉ እቅድ ይዞ የነበረ ሲሆን የጽ/ቤቱ የበላይና መካከለኛ አመራርም በችግኝ ተከላው አካሂደዋል፡፡የጽ/ቤቱ ሠራተኞችም በቀጣይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት በሰራተኞች የችግኝ ተከላ ያካሂዳል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራርና የሜኔጅመንት አባላት በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተሳተፉ