News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ከግሎባል ኤሲአይ (Global ACI) ጋር ያለውን የባለብዙ ወገን የጋራ እውቅና ስምምነት በፊርማ አደሰየኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የአለምአቀፍ ዕውቅና ትብብር (GLOBAL ACCREDITATION COOPERATION INCORPORATED) ሙሉ አባል ሆነ::በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ግዜ ከነሐሴ 24-29/2017 ዓ.ም እየተካሄደ የሚገኘው ‘የኢትዮጵያ ይግዙ ‘ የንግድ ሳምንት ላይ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ለጎብኝዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡Call for Healthcare Accreditation Surveyorየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የኢስኳ ISQua ይፋዊ ሙሉ አባል በመሆን አለም አቀፍ የጤና ዘርፍ አክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት መስጠት የሚያስችለውን እውቅና አጊንቷል።የኢትዮጵያ አክሬድቴሽን አገልግሎት 17ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን አከበረ።የመ/ቤቱ ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱጥራትን ማስጠበቅ የሁሉም አካላት አንገብጋቢ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠ

ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ

*******************************************************************

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ በግብርና ምርቶች ኢንስፔክሽን ዘርፍ በሁለት ምርቶች እና በአራት ወሰኖች ላይ የአክሬዲቴሽን ዕውቅና ሰጠ።

በዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦንሳ ባይሳ ጎሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቪስ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎትን መርጠው አክሬዲት በመሆናቸው አመስግነዋል።

አክሬዲቴሽን ዓለም አቀፍ ሥርዓት መሆኑን የገልጹት ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ ካላቸው ሃገራት ተርታ ይመደባል። በዓለም ተወዳዳሪ ለመሆን የጥራት ጉዳይ መሰረታዊ ነው። ለዚህም አክሬዲቴሽን እንደቪዛ በመሆን እንደሚያገለግል ገልጸዋል።

የግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ ብሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ከመመስረቱ በፊት የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ለማግኝት ይቸገሩ እንደነበረ ገልጸው የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የግብርና ምርቶቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ገለጸው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በቀጣይም በአውሮፓ ገበያዎች ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችሉ ተጨማሪ የአክሬዲቴሽን አገልግሎቶች እንዲሰጣችው ጥያቄ አቅርበዋል።

አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠ