News

ነሀሴ 29 ቀን 2015ዓ.ም

አዲስ አበባ

አቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ሹመታቸውን ተከትሎ በአገልግሎቱ ዋና ዳይሬተር ቢሮ በመገኘት ከአገልግሎቱ የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ እና የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

አገልግሎቱ ያለበትን ደረጃ እና በ2015 በጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እንዱሁም በቀጣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ የአገልግሎቱ የዋና ዳይሬከተር ተወካይ በመሆኑ ላለፉት ሁለት ወራት ያገለገሉት የአገልግሎቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ውብታየሁ ባቲ ሰፊ ያለ ማብራሪያ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በዚህም መሰረት ከዓለም አቀፍ አቻ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙት በማጠናከር ዓለም አቀፍ ዕውቅና የማስቀጠል ስራዎች፣የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ ዝግጅት፣የአገልግሎቱ የሰው ሃይል አደረጃጀት፣አዲስ በመገንባት ላይ ያለው የአገልገሎቱ ሕንጻ ያለበትን ደረጃ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች በማብራሪያው  ተዳሰዋል፡፡

ማብራሪያውን ተከትሎ በቀጣይ መሰራት ያለባቸው ስራዎች እና የትኩረት አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ ሁሉም የስራ አመራር አባላት ስራዎቻቸውን በኃላፊነት ስሜት እንዲወጡ ያሳሰቡት ዋና ዳይሬከተሩ እንደ መሪ ከእሳቸው የሚጠበቁ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ እንዱሁም የሚጠበቅባቸውን የአመራር ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ዋና ዳይሬክተሩ ከአገልግሎቱ አመራር አባላት እንዲሁም  ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር  እና ከተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች ጋር በመሆን “የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የውሃና ኢነርጂ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

በአውደ ርዕዩ ላይ የውሃ ሃብታችን ጥራቱን የጠበቀና ለሚፈለገው አገልግሎት፣ ለመስኖ፣ ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለመዝናኛ እንዲሁም ለግድብና ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል ለማስቻል ሚ/ር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ዘመናዊ የውሃ ጥራት ማስጠበቂያ መሳሪያዎችን ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑንም  መመልከት ተችሏል፡፡  

አቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ