=============================
አዲስ አበባ 10/11/ 2015
ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን በላይ ችግኝ የመትከል መርሐ ግብሯን ማሳካቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
የተዛባ አየር፣ የተራቆተ ምድር ለትውልድ አናወርስም ብላችሁ፤ ጎሕ ሳይቀድ ወደ ተራሮችና ሸለቆዎች፣ ወደ ሜዳዎችና ሸንተረሮች ተሠማርታችሁ 566 ሚልዮን ዛፎች መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በዚህም መሰረት አገራዊ ጥሪውን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመገኘት የአረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር የታሪኩ ተጋሪ መሆን ችለዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ላይ አገልግሎቱን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተው ሐምሌ 05 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ በቅርቡ ስራቸውን የለቀቁት የአገልግሎቱ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡ