ሚያዝያ 05 ቀን 2015ዓ.ም የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ከሚሰጣቸው የአክሬዲቴሽን አገልግሎቶች መካካል የሕክምና ላቦራቶሪ አክሪዲቴሽን ISO 15189:2012 ን አዲስ በተከለሰው ISO 15189:2022 ለመተካት እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ የሽግግር ዕቅድ አዘጋጀ፡፡ በዚህም መሰረት አገልግሎቱን ለሚፈልጉ አዲስ አመልካቾች ከመስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ በተከለሰው ISO 15189:2022 የሚስተናገዱ መሆኑን አግልግሎቱ አስታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ቀደም ብለው አገልግሎቱን ለማግኘት እዉቅና ያገኙ እንዲሁም በሂደት ላይ ያሉ ደንበኞች ከሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በኃላ አሰስመንት የሚከናወነው አዲስ በተከለሰው መሰረት ISO 15189:2022 እንደሚሆን የአገልግሎቱ የጥራት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ አየለ ገልጸዋል፡፡ አክለውም የሕክምና ላቦራቶሪ የተሰማሚነት ምዘና ተቋማት የተከለሰውን አዲሱን የህክምና ላቦራቶሪ ደረጃ ISO 15189:2022) የሽግግር ዕቅዱ ዝርዝር ይዘት ከአገልግሎቱ ድረ-ገጽ ላይ https://eas-eth.org/forms/ በማውረድ ማስተካከያዎችን በማድረግ ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀ admin April 13, 2023February 22, 2024 Announcements, Uncategorized