News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠየዜና መግለጫየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በምርት ሰርቲፊኬሽን እና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘአቶ ቦንሳ ባይሳ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ የአገልግሎቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የበኩላቸውን ተወጡየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አዲሰ በተከለሰው የሕክምና ላቦራቶሪዎች ደረጃ ለመተግበር የሽግግር እቅድ አዘጋጀEthiopian Accreditation Service top management and technical staffs visited Quality Council of Indiaየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት እንደሃገር የመጀመሪያውን የምርት ሰርተፊኬሽን እና በግሉ ዘርፍ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ጨምሮ አጠቃላይ ለ11 ተቋማት የላቀ ብቃት የሶስተኛ ወገን ምስክርነት የአክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት ሰጠ፡፡የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የስድስት ወር አፈጻጸም እየገመገም ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ጋር የ127ኛውንየአድዋ ድል በዓልን የካቲት 22 ቀን 2015ዓ.ም በኢትዮጵያ ደረጃዎቸ ኢንስቲትዩት አዳራሽ በውይይት አከበሩ፡፡

ከመከላከያ ሚ/ር ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ127ኛውን የአድዋ ድል በዓልን የተመለከተ የመወያያ ጽሁፍ ግልጽ ሆኖ የተዘጋጀ መሆኑን በመግለጽ ተሳታፊዎች በጥሞና በመከታተልና ተሳትፎ በማድረግ ለቀጣን በምናደረገው የብልጽግና ጉዞ ትምህርት በመቅሰም የምንጠቀምበት መሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዱ አባጊቤ (ዶ/ር) መልዕክት በማስተላለፍ ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ስልጣኔና አኩሪ ታሪክ ባለቤት ስትሆን በረጅም ዘመን ታሪኳ ጎልተው እና ደምቀው ከሚታወቁና ከሚታወሱ በርካታ የታሪክ ሁነቶች መካከል አንዱ የአድዋ ድል ነው፡ ፡ይህ ታላቅ ድል የሆነው ለ127ኛ ጊዜ ሲከበርና ሲዘከር የጦርነቱን መንስኤዎች፣ የኢትዮጵያውያንን የዲፕሎማሲ ትግል፣ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ለነጻነት የከፈሉት መስዋዕትነት፣ የድሉን ትሩፋቶች ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳዎችን ለአሁኑ ትውልድ በሚገባ ማስገንዘብ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን በአገልግሎቱ ህዝብ ግንኙነትና ኩሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ መሐመድኑር ከማል ገለጻ ቀርቧል፡፡

በውይይቱ ላይ የአሁኑ ትውልድ አድዋን ድል ካደረጉ አባቶቻችን ትምህርት ወስዶ አንድነቱን በማጽናት ድህነትን ታግሎ ማሸነፍ እንደሚጠበቅ የገለጹ የስብሰባው ተሳታፊ ጣሊያንን አድዋ ላይ ድል ያደገረ አገር ሕዝብ ዛሬ የድህነት ታሪክን ለትውልድ ማሸጋገር የለበትም ሲሉ አክለዋል፡፡

የአድዋ ድል ለሰው ዘር ሁሉ በተለይም ለጭቁን ሕዝቦች ትልቅ ትምህርት ያበረከተ ቢሆንም ታሪክን መዘከር ብቻ ሳይሆን ታሪክን ሰርተን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ እንዳለብን የሰብሰባው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

ለአገራችን ሉዓላዊነትና ሁለተናዊ ዕድገት በብሄር እና በሃይማኖት ሳንከፋፈል መስራት እንደሚጠበቅብን በመገለጽ አገርንና ሕዝብ በመከፋፈል ለመበታተን የሚሰሩ አካላትን በጋራ መታገል እንደሚገባ አብዱ አባጊቤ(ዶ/ር) አሳስበዋል፡፡

ከድህነት በመውጣት ወደብልጽግና ልንጓዝ የምንችለው አመራሩም ሰራተኛውም ከብሄር እና ከሐይማኖት ጽንፈኝነት መላቀቅ እና በአንድነት መቆም ስንችል ብቻ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በዓሉም በመላ ሃገሪቱ “የ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ለአገራዊ አንድነት፣ ጀግንነት እና ጽናት መህልቅ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

የአገልግሎቱ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢትስቲትዩት ሰራተኞች ጋር የ127ኛው የአድዋ ድል በዓል በውይይት አከበሩ