News

ጥር 01 ቀን 2015ዓ.ም

በንግድና ቀጠናዊ ትስሰር ሚኒስቴር የጥራት መሰረተ-ልማት ዘርፍ የሥራ አመራር እና የዘርፉ ተጠሪ ተቋማት የ2015 የመጀመሪያውን ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡

በአዳማ ኃይሌ ሪዞርት ሆቴል ጥር 01 ቀን 2015ዓ.ም በተካሄደው ውይይት ላይ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ የአገልግሎቱን አፈጻጸም ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንደገለጹት በአገልግሎቱ ባለፉት 6 ወራት በሜዲካል፣ በፍተሻ፣በኢንስፔክሽን እና በሰርቲፊኬሽን በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰረት አገልግሎቱ ለተለያዩ 08 አዲስ የተስማሚነት ምዘና አካላት የአክሪዲቴሽን አመልካቾች የሶስተኛ ወገን መስክርነት ዕውቅና በ2015 ዓ.ም ግማሽ አመት ውስጥ የተሰጣቸው መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በግሉ ዘርፍ እንደሃገር የመጀመሪያው የሆነው ዊነር ካሊብሬሽን ላቦራቶሪ እንደተሰጠው አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም አገልግሎቱ በምርት ሰርቲፊኬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሰጠ ሲሆን የድርጅቱ አመራሮች እና ባለሙያዎች ለዚህ ስኬት ላደረገት አስተዋጽዖ አመስግነዋል፡፡

በተመሳሳይ ሌሎች የዘርፉ 3 ተጠሪ ተቋማት እና የሚኒስቴር መ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎቻቸው የተቋሞቻቸውን የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

የሚኒስቴሩ የጥራት መሰረተ-ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር አቶ እንዳለ መኮንን የሁሉንም ተቋማት ሪፖረት የገመገሙ ሲሆን የተጠሪ ተቋማት ቅንጅታዊ ስራ እራስን የማስተዋወቅ ስራ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸው ከተለዩ የስራ አመራር አባላት ላነሱት ጥቄዎች ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል፡፡

የሚኒስቴሩ የጥራት መሰረተ-ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር አቶ እንዳለ መኮንን
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተሰማ
በንግድና ቀጠናዊ ትስሰር ሚኒስቴር የጥራት መሰረተ-ልማት ዘርፍ የመጀመሪያውን ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ