News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ሠራተኞች ዛሬ ለመከላከያ ክብር እቆማለሁ በሚል መሪ ቃል በኪነጥበብ ባለሙያዎች አስተባባሪነት በመላ ሃገሪቱ የተዘጋጀውን ፕሮግራም መሰረት በማድረግ ለመከላከያ ሰራዊቱ  ያላቸውን ክብርና ድጋፍ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በግራ እጅ በመያዝና ቀኝ እጃቸውን በደረት በማድረግ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለአንድ ደቂቃ ለመከላከያው ያላቸውን ክብርና ድጋፍ ለአንድ ደቂቃ በማጨብጨብ የገለፁ ሲሆን መከላከያው የዜጎችን ሰላም ለማስከበር እያደረገ ያለውን ሰላም የማስከበር ዘመቻም እንደሚደርፉ በዚሁ ጊዜ ተገልጿል፡፡

ለመከላከያ ክብር እቆማለሁ በሚለው በዚሁ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ እና የብሔራዊ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች በጋራ አካሂደዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን ክብርና ድጋፍ ገለፁ: