News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ዳይሬክትሬት ጽ/ቤት በተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር ኢንፎርሜሽን ስርአትና እና በሌሎች ርዕሶች ላየ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡በጽ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክትሬት የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የኮቪድ ወረርሽኝን ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን ሥልጠናው የሥራ ክፍሎች ዓመታዊ የግ» እቅድ ሲያዘጋጁ በተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር ኢንፎርሜሽን ስርአትና /ኢፍሚስ/ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ያቀደ ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪ የጽ/ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፖሊሲ መሰረት ያደረገ የጽ/ቤቱ የኢሜል አጠቃቀም ላይም ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ለመንግስት ሥራ ማንኛውም የጽ/ቤቱ ሠራተኛ የግል ኢሜል መጠቀም እንደማይችልና ይህም በፖሊሲው የተቀመጠ በመሆኑ የጽ/ቤቱን ኢሜል ብቻ ሊጠቀም እንደሚገባ አሰልጣኙ አቶ አዱኛ አብዲሳ አሳስቧል፡፡ስልጠናው ለሥራ ክፍሎች በተለያዩ ቀናት የተዘጋጀ ሲሆን መስከረም 12 ቀን 2013ዓ.ም ለጽ/ቤቱ የአክሬዲቴሸን ዳይሬክትሬት ባለሙያዎች እንዲሁም መስከረም 13ቀን 2013ዓ.ም ከተለየዩ የሥራ ክፍል ሃለፊዎች ተሰጥቷል፡፡

ጽ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተሬት ለውስጥ ሰራተኞች ስልጠና እየሰጠ ነው