የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት ለሁለት ወላጅ አልባ ሕጻናት የትምህርት መገልገያ ደብተር እና ቦርሳ እንዲሁም ጫማና የስፖርት ልብስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ጽ/ቤቱ ድጋፍ ያደረገው የ2013ዓ.ም የትምህርት ዘመን መጀመርና አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድርግ ሲሆን ድጋፍ ያደረገላቸው ታዳጊዎች ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በጽ/ቤቱ ከሰራተኞች በሚሰበሰብ ገንዘብና ከጽ/ቤቱ በሚደረግ አነስተኛ ድጋፍ የሚደገፉ ናቸው፡፡
ጽ/ቤቱ ከትምህርት ቁሳቀዩሱና ከዓልባሳቱ በተጨማሪ ለአዲሱ ዓመት በዓልም ለያንዳንዳቸው የ800 መቶ ብር የገንዘብ ድጋፍ ሰጥቷል፡፡
ጽ/ቤቱ ሕፃናቱ የ2ኛ ክፍል ተማሪ እያሉ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፍ እያደረገላቸው ያሉት ተማሪዎች ሲሆኑ በዓመቱ መጀመሪያና በዓመቱ አጋማሽ ላይ እገዛዎችን ሲያደርግላቸው ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ሁለቱም ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሆነዋል፡፡
ለተማሪዎቹ እገዛ ሲደረግ ተማሪዎቹ በትምህርታቸው እንዲጠነክሩ ያበረታቱዋቸው የጽ/ቤቱ የሴቶች ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ አዜብ ሰለሞን ጽ/ቤቱ በቀጣይም አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፉን እንደሚቀጥል ጠቅሰው ተማሪዎቹ በትምህርታቸው በመጠንከር የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርጉ መክረዋል፡፡
ጽ/ቤቱ ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ የጀመረውን ድጋፍ እንዳማያቋርጥም ተገልጿል፡፡
ጽ/ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሁለት ወላጅ አልባ ህፃናት ድጋፍ አደረገ፡