News
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ከግሎባል ኤሲአይ (Global ACI) ጋር ያለውን የባለብዙ ወገን የጋራ እውቅና ስምምነት በፊርማ አደሰየኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የአለምአቀፍ ዕውቅና ትብብር (GLOBAL ACCREDITATION COOPERATION INCORPORATED) ሙሉ አባል ሆነ::በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ግዜ ከነሐሴ 24-29/2017 ዓ.ም እየተካሄደ የሚገኘው ‘የኢትዮጵያ ይግዙ ‘ የንግድ ሳምንት ላይ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ለጎብኝዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡Call for Healthcare Accreditation Surveyorየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የኢስኳ ISQua ይፋዊ ሙሉ አባል በመሆን አለም አቀፍ የጤና ዘርፍ አክሬዲቴሽን ሰርተፍኬት መስጠት የሚያስችለውን እውቅና አጊንቷል።የኢትዮጵያ አክሬድቴሽን አገልግሎት 17ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን አከበረ።የመ/ቤቱ ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱጥራትን ማስጠበቅ የሁሉም አካላት አንገብጋቢ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በልዩ ልዩ መስኮች ዓለም አቀፍ  እውቅና አገኘ፡፡አገልግሎቱ ለግሎባል ኢንስፔክሽን ሰርቬይ ኤጀንሲ ዕውቅና ሰጠ

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በሥሩ የሚገኙ 15 ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እና የሥራ ሃላፊዎች በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የችግኝ ተከላ አካሔዱ፡፡ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ ለሚ በተካሔደው የችግኝ ተከላ ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስተሩ ክቡር አቶ መላኩ አለበል የችግኝ ተከላው በተካሔዱበት ቦታ ባስተላለፉት መልዕክት የሚኒስቴር መሥሪያቤቱ በመላ ሃገሪቱ 20 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ የያዘ ሲሆን ለዚህም ሥራ ከክልል መስተዳድሮች ጋር በመነጋገር ላይ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ቦታ ተረክቦ ሥራው መጀመሩንና የችግኝ ተከላ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡በቦሌ ለሚ በተካሔደው ሚኒስቴሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተሳተፉበት በዚህ የችግኝ ከተላ 2 ሺህ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን የተናገሩት ሚኒስተሩ በቀጣይ እያንዳንዱ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተጠሪ የሆነ ተቋም የሚኒስቴር መሥሪያቤቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት ከሰራተኞቹ ጋር የግኝ ተከላ ያካሂዳል ብለዋል፡፡በዚህ የችግኝ ተከላ ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች እና ምክትል ዋና ዳይሬከተሮቸ እንዲሁም ዳይሬክተሮች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴረና ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ አካሔዱ