News

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ማኔጅመንትና የቴክኒክ ባለሙያዎች የአገልግሎቱን ፖሊሲዎችና ዓላማዎች በአግባቡ ተረድተው አገልግሎቱን ሲሰጡ በእውቀት ላይ ተመስርተው ሊሆኑ እንደሚገባ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ገለፁ

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አርአያ ፍስሃ ዛሬ የካቲት 16ቀን 2014ዓ.ም በአዳማ በተጀመረው የአገልግሎቱ የማኔጅመንትና የቴክኒካል ባለሙያዎች ISO/IEC 17011:2017 በዓለም አቀፉ ደረጃ ላይ በተጀመረው ስልጠና ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ለሌሎች ተቋማት ሶስተኛ ወገን በመሆን ዓለም አቀፍ ምስክርነት የሚሰጥ በመሆኑ ራሱ አስቀድሞ ዓለም አቀፉን ደረጃ በሚገባ ሊረዳ ይገባል

ብቃት በአንድ ቀን የሚገነባ አይደለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ላለፉት ዓመታት ተቋሙ በደረጃዎች ላይ አቅም ሲገነባ መቆየቱን ጠቁመው የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት የቴክኒካልና የሜኔጅመንት አባላትም የአገልግሎቱን ፖሊሲና ዓላማ በአግባቡ ተረድተው ለሌሎች ማስረዳትና ማብራራት ይገባቸዋል ብለዋል

የቴክኒካል ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በአግባቡ ተረድተው ሊተረጉሟቸው ይገባል ያሉት አቶ አርአያ የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን ለመስጠት አንድ ጊዜ ብቻ ተሰርቶ የሚያልቅ ሳይሆን በየወቅቱ እያደገ የሚሔድ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ደረጃው በትክክል ለመታየት መቻሉን መረጋገጥ ይገባል ብልዋል

በዓለም አቀፍ ደረጃው ላይ ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ጽጌ መላክ በስልጠናው ላይ እንደገለጹት ስልጠናው በዋናነት በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት አገልግሎቱ ዓለም አቀፍ ደረጃ ግምገማ የሚደረግበት በመሆኑ ይህንን መሰረት አደርጎ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ISO/IEC 17011:2017 በቂ እውቅት እነዲኖር ለማድረግ ነው

በዓለም አቀፉ ደረጃ ላይ መሰጠት የተጀመረው ስልጠና ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም የአገልግሎቱ የማኔጅመንት አባላትና የቴክኒክ ባለሙያዎች በስልጠናው ላይ ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ስልጠናው መመዘኛ እንደሚኖረውም በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገልጿል

ስልጠናውን የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልገሎት ዋና ደይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጌተንት ጽጌመላክና የጥራት ሥራ አስኪያጅዋ ወ/ሮ መሰረት ተሰማ የሚሰጡት መሆኑን በፕሮግራሙ ላይ ተመልክቷል

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ፖሊሲዎችንና ዓላማዎችን በደንብ መረዳት እንደሚገባ ተገለፀ