News

EAS  ጥቅምት 4 /2017 ዓ.ም

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!”  በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀ-ግብሮች በድምቀት አክብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አክሬድቴሽን አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞችም ሁነቱን ታድመዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሰንደቅ ዓላማ የጋራ ዓላማችን ሰንደቅ ማሳያ ምልክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያዊ ዓላማና በህብረ-ብሄራዊ አንድነት የደመቀ፣ በአብሮነት የጎመራ ብልጽግና የተረጋገጠበት ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ትልም ለሀገርና ህዝብ ይዘን  እየተንቀሳቀስን ብለዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም ለህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለሀገራዊ የከፍታ ጉዞ አብይ ምልክት ሰንደቅ ዓላማችን  መሆኑን በመጥቀስ ሰንደቅ ዓላማ አንድ ያደረገውን ህዝብ ምንም ጉዳይ ሊለያየው እንዳማይችል አንስተዋል።  ለሰንቅ ዓላማ ክብር አያት ቅድመ አያቶቻችን ባደረጉት ተጋድሎ በነጻነት እንድንኖር ያደረገን መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ የበለጠ ከፍ እንዲል ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ ቃሉን አድሶ ለበለጠ ውጤት መትጋት እንዳለበት ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

Once Accredited Accepted Everywhere !

tel: +251-116671247/0116670995
Web: www.eas-eth.org
Facebook: https://web.facebook.com/enaoETH.
Twitter : ( X ) @Enao-ETH
Email: info@eas-eth.org
P.O.Box – 3898

የኢትዮጵያ አክሬድቴሽን አገልግሎት 17ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን አከበረ።