የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ለኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን በኢንስፔክሽን ዘርፍ የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ሰጠአገልግሎቱ ለባለስልጣኑ መሥሪያቤት በኢንስፔክሽን ዘርፍ ISO/IEC 17020 በመድሃቲት ተቋማት ኢንስፔክሽን የአክሪዲቴሸን አገልግሎቱን የሰጠ ሲሆን የባለስልጣኑ መሥሪያቤት በዚህ ዘርፍ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ በመሆኑ በተለይ መንግስት በሕክምናው ዘርፍ የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል እያደረገ ያለውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝ ተጠቁሟልለባለስልጣኑ መሥሪያቤት የአክሪዲቴሽን ሰርቲፍኬት የአሰጣጥ ስነ ስርአት ላይ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ባስተላለፉት መልዕክት የአክሪዲቴሽን አገልግሎት እንደ ሃገር ብዙ ሊሰራበት የሚገባና የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነውየኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን በመድሃኒት ተቋማት ኢንስፔክሽን ዘርፍ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ መሆኑ እጅግ የሚያበረታታ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው ባለስልጣኑ የመድሃኒትን ጥራት፣ ፈዋሽነትና ደህንነት ለመቆጣጠር የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑና እውቅና መግኘቱ ትልቅ ውጤት እንደሆነ ጠቁመዋልመንግስት በቀጣይ ባለስልጣኑ በሌሎች ዘርፎችም የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ለማግኘት በሚያደርግው ጥረት ውስጥ እገዛ እንዲያደርግም አብራርተዋልየኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ት ሔራን ገርባ በበኩላቸው ባለስልጣኑ ISO/IEC 17020 በመድሃኒት ኢንስፔክሽን ያገኘው የአክሪዲቴሸን ዓለም አቀፍ እውቅና ተቋሙ ለሕብረተሰቡ በመድሃኒት ኢንስፔክሽን እየሰጠ ያለው አገልግሎት የበለጠ ተአማኒ ያደርግዋልባለስልጣኑ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት በዘርፉ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ተቋም የመሆን ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተርዋ የተቋሙ ራዕይ አሁን ሲታይ ሩቅ ቢመስልም ባለስልጣኑ ግን ይህን ለማሳካት ይሰራል ብለዋልተቋሙ ከአሁን ቀደም የምግብ ጥራት ላቦራቶሪን ወደ አክሪዲቴሸን ማስገባቱንና በአሁኑ ወቅትም ISO/IEC 17025 በፍተሻ ላቦራቶሪ በአስራ አንድ የፍተሻ ወሰኖች የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ለማግኘት እየሰራ ነው ብለዋልየኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ ለባለስልጣኑ መሥሪያቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ት ሔራን ገርባ የአክሪዲቴሸን ሰርቲፍኬቱን ከሰጡ በኃላ ባደረጉት ንግግር አክሪዲቴሽንን ተግባራዊ ለማድግ የተቋም አመራር ቁርጠኝነት ይጠይቃልአክሪዲቴሸን የሰርቲፍኬት ስጦታ አይደልም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አክሪዲቴሽን ብቃትን የሚለካና የሶስተኛ ወገን ማረጋገጫ ሲሆን አንድ ተቋም የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ሲሆን ተቋሙ የአሰራር ስርአት መዘርጋቱ፣ የሰነድ ዝግጅቱ በተግባር የሚያከናውናቸው ሥራዎችና የባለሙያዎች ብቃት ይፈተሻል ብለዋልተቋሙ ያገኘውን የአክሪዲቴሽን አስጠብቆ መቆየት እንደሚገባው የተናገሩት አቶ አርአያ የአክሪዲቴሸን አገልግሎት በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሰጠው አክሪዲቴሽን በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የክትትል አሰስመንት እንደሚሰራም ገልጸዋልየአክሪዲቴሸን አገልግሎት ባለፉት አስር አመታት አገልግሎቱን ከመስጠት ጎን ለጎን ራሱን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስገምገም የፍተሻ ላቦራቶሪ ISO/IEC 17025 በሕክምና ላቦራቶሪ ISO 15189 እንዲሁም በኢንስፔክሽን ISO/IEC 17020 ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቱንና በስርዓት ሰርቲፍኬሸን ISO/IEC 17021 በዓለም አቀፍ የገምጋሚዎች ቡድን ተገምግሞ ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት እየጠበቀ ነው ብለዋልየኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት ለኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዛሬ መጋቢት 1ቀን 2014ዓ.ም የአክሪዲቴሸን ሰርቲፍኬት አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሥራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል
የኢትዮጵያ አክሪዲቴሸን አገልግሎት (EAS-Ethiopian Accreditation Service)ለኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን( Ethiopian Food and Drug Authority /EFDA/ የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ሰጠ