News

የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የፕሮፊሸንሲ ቴስቲንግ ችግርን መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ፕሮፊሰንሲ ቴስቲ ከታክስ ነጻ የሚሆንበት መንገድም ሊታሰብ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት የትርፍ ሰአት አሰሰሮች ተናገሩአሰሰሮቹ ሐምሌ 4 እና 5 ቀን 2013ዓ.ም በአዳማ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የአሰሰሮች ዓመታዊ ኮንፍረንስ ላይ እንደተናገሩት የአክሪዲቴሸን አገልግሎት ባለፉት ዓመታት እያደገና እየሰፋ የመጣ ቢሆንም አሁንም የሚፈለገው ደረጃ እንዲደርስ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎች ሊፈቱ ይገባልተቋማት ወደ አክሪዲቴሸን እንዳይመጡ ዋናው ምክንያት የፕሮፊሸንሲ ተዌስቲንግ PT /ወይንም ለንጽጽር የሚሆን ውጤቱ የታወቀ ናሙና/ ጉዳይ መሆኑን የተናገሩት አሰሰሮቹ ሰርቲፋይድ ሪፈረንስ ማቴርያልና የፒቲ /CRM and PT/ ጉዳይ በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋልጽ/ቤቱ በባለሙያ ስልጠና በሰነድ ዝግጅትና ባለፉት ዓመታት የአክሪዲቴሸን አገልግሎትን በመስጠት ረገድ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች እንደሆኑ የጠቆሙት አሰሰሮቹ ሆኖም አክሪዲቴሽን የበለጠ ጥቅም እንዲኖረው የሃገሪቱ መርቶች በዓለም ገበታ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አክሪዲቴሸን ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት በአስፈፃሚው አካል ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባልተቋማት ወደ አክሪዲቴሸን እንዲመጡ አክሪዲቴ በሆኑና ባለሆኑ ተቋማት መካከል ልዩነት ሊኖር ይገባል ያሉት አሰሰሮቹ አሁን ሁለቱም እኩል የሚታዩ በመሆኑ አክሪዲቴሸን ጎልቶ ሊወጣ አልቻለም ብለዋል አክሪዲቴሸን ውጤታማ እንዲሆን ከሚያደረግት ነገሮች የባለሙያዎች ብቃት እንደሆነ የጽ/ቤቱ የትርፍ ሰዓት አሰሰሮች ጠቁመው ባለሙያዎችም በዘርፉ የተሻለ ጥጠቅም የሚያገኙበትን ሁኔታ ማሰብ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋልበዚሁ በዓመታዊ የአሰሰቶች ኮንፍረንስ ላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለይም በኮቪድ 19 ወረርሺኝን ተከትሎ በ2012 ዓ.ም ዓመታዊ የአሰሰሮች ካሊብሬሸን አለመካሔዱና በዚህ ወቅት አዲስ በተዘጋጁና በተከለሱ ሰነዶች በመኖራቸ ውይይት ማድርግ በማስፈለጉ መድረኩ መዘጋጀቱ ተመልክቷልበሁለቱ ቀን ውይይት ላይ የተለያዩ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የአክሪዲቴሸንን ሂደት የተመለከተ፣የአክሪዲቴሸን አገልግሎት የጊዜ ሰሌዳ፣የተስማሚነት ምዘና ተቋማት ግዴታዎች፣የአክሪዲቴሸን ስምምነት፣የኢትይጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት እና የዓለም አቀፉ የላቦራቶሪ አክሪዲቴሸን ትብብር ሲምቦል አጠቃቀም፣ እንዲሁም በፕሮፊሸንሲ ቴስቲንግና በትሬሰብሊቲ ጉዳዮች ላይ በሰነዶች ላይ አዲስ የተደረጉ ለውጦችን አስመልክቶ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተድርጎባቸዋል

የአክሪዲቴሽን አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የፕሮፊሸንሲ ቴስቲንግ ችግርን መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል::