News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ለሚገኙ የሕክምና ተቋማት ISO 15189 የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ጽ/ቤቱ ሚያዚያ 11ቀን 2013ዓ.ም በአዳማ ጀርመን ሆቴል የጀመረው ስልጠና የሕክምና ተቋማት ለሕብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት የበለጠ ተአማኒና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ላቦራቶሪዎቻቸውን ወደ አክሪዲቴሽን እንዲያመጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መዘጋጀቱን የጽ/ቤቱ የጥራት ሥራ አስኪያጀ ወ/ሮ መሰረት ተሰማ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው ተቋማቱ ዓለም አቀፍ መስፈርቱ ተረድተው በተቋሞቻቸው ተግባራዊ ሊያደርጓቸው የሚገቡ አሰራሮችን እንዲተገብሩና በሂደት ወደ አክሪዲቴሸን እንዲመጡ ለማደርግ ዓላማ እንዳለው የጥራት ሥራ አስኪያጅዋ ጠቁመው ጽ/ቤቱ ተቋማት በስልጠና ረገድ ያለባቸውን ክፍተት ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው ላይ በአካማ ከተማ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ሆስፒታሎች፣ከፍተኛና መካከለኛ ክኒሊኮች የላቦራቶሪ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ጽ/ቤቱ ለሕክምና ተቋማት የፍተሻ ላቦራቶሪዎች ስልጠና እየሰጠ ነው