News

የኢትርዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ተቋማት በአክሪዲቴሸን ዙሪያየተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድርግ በኮምቦልቻና የደሴ ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ጽ/ቤቱ መጋቢት 8 እና 9 ቀን በኮምቦልቻ እንዲሁም መጋቢት 13 እና 14 ቀን 2013 ዓ.ም በደሴ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጠ ሲሆን የአክሬዲቴሸን  ጠቃሜታ ተገንዝበው የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ እንዲሆኑና ለሕብረተሰቡ የሚሰጡትም አገልግሎት ተአማኒና ተቀባይነት እንዲያገኙ ለማስቻል ነው፡፡

ተቋማት ስለ አክሪዲቴሸን በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው በሕክምናና በፍተሻ ላቦራቶሪ፣በኢንስፔክሽን፣በሰርቲፍኬንንና ዘርፍ የአክሪዲቴሸን ተጠቃሚ ቢሆኑ በሚያወጧቸው ሪፖርቶች፣በሚሰጡዋቸው የፍተሻ አገልግሎቶችና በሚያካሂዱት የኢንስፔክሽን  ሥራ የሚኖራቸው ተአማኒነትና ተቀባይነት እንደሚያድግ በስልጠናው ላይ ተገልጿል፡፡

አክሪዲቴሽን የአሰራር ስርአትን በመዘርጋት የድግግሞሽ ሥራን ለማስቀረትና ከስህተት የጸዳ ሥራ ለመስራት ከፍተኛ እገዛ እንዳለው በስልጠናው ላይ የተገለፀ ሲሆን የተስማሚነት ምዘና ተቋማት ወደ አክሪዲቴሽን ቢመጡ ለተቋማቸውም ሆነ አገልግሎት ለሚሰጡት ሕብረተሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተብራርቷል፡፡

በሁለቱ ከተሞች በተካሔደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት፣ዩኒቨርስቲዎችና ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በቀጣይ በአዲስ አበባ ለሕክምና ላቦራቶሪዎች ISO 15189 የሁለት ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይካሔዳል፡፡

ጽ/ቤቱ በኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ