News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሸን ጽ/ቤት ሠራኞቹና የማኔጅመንት ዛሬ ጥር 18 ቀን 2013ዓ.ም በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ  የአረንጓዴ ስፍራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

በጉብኝቱ የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ይስማ ጅሩ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ኤጀንሲው ከክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላለፈውን መልዕክት መሰረት አድርጎ በግቢው ውስጥ የነበረውን ቦታ በግሪን ሀውስ በመጠቀም የተለያ የጓሮ አትክልቶችን በማምረት ሰራተኛው በተመጣይ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆን እያደረገ ነው፡፡

ማህበረሰቡ በአካባው ባለው ጥቂት ቦታ የጓሮ አትክልቶችን በማምረት ቢጠቀም በኢኮኖሚም ሆነ በጤና ረገድ ተጠቃሚ እነደሚሆን የተናገሩት አቶ ይስማው ኤጀንሲው የተቋሙ ሰራተኞች በቤታቸው ተመሳየ ሥራ እነዲሰሩ ያበረታታል ይደግፋል ብለዋል፡፡

ኤጀንሲወ ተሞክሮውን ለመንግስት ተቋማተና ለተለያ የህብረተሰብ ክፍሎች እያካፈለ እነደሆነም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት ሠራኞችና ሜኔጅመንት የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ የአረንጓዴ ተክሎች ቦታን ጎበኙ፡፡