News

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በሥሩ የሚገኙ 15 ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እና የሥራ ሃላፊዎች በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የችግኝ ተከላ አካሔዱ፡፡ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ ለሚ በተካሔደው የችግኝ ተከላ ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስተሩ ክቡር አቶ መላኩ አለበል የችግኝ ተከላው በተካሔዱበት ቦታ ባስተላለፉት መልዕክት የሚኒስቴር መሥሪያቤቱ በመላ ሃገሪቱ 20 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ የያዘ ሲሆን ለዚህም ሥራ ከክልል መስተዳድሮች ጋር በመነጋገር ላይ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ቦታ ተረክቦ ሥራው መጀመሩንና የችግኝ ተከላ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡በቦሌ ለሚ በተካሔደው ሚኒስቴሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተሳተፉበት በዚህ የችግኝ ከተላ 2 ሺህ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን የተናገሩት ሚኒስተሩ በቀጣይ እያንዳንዱ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተጠሪ የሆነ ተቋም የሚኒስቴር መሥሪያቤቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት ከሰራተኞቹ ጋር የግኝ ተከላ ያካሂዳል ብለዋል፡፡በዚህ የችግኝ ተከላ ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የተቋማት ዋና ዳይሬክተሮች እና ምክትል ዋና ዳይሬከተሮቸ እንዲሁም ዳይሬክተሮች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴረና ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ አካሔዱ